የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆማቸውን ለማረጋገጥ በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ስለሚያደርጉ መንገዶች ይዘጋጋሉ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ በመስቀል አደባባይ ሊሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል

(ኢዜአ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ በመስቀል አደባባይ ሊሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

በነገው እለት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ‘ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆማቸውን ለማረጋገጥ በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ያደርጋሉ፡፡

ለዚህም ሰልፉ ስኬታማ እንዲሆን የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን እና በእለቱ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም እና ለመከላከያ ሰራዊት እና ለሌሎች የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለተሰማሩ የፀጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ ነው ተብሏል ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነዋሪዎቹ የሰራዊታችን ደጀን መሆናቸውን ለማሳየት የሚያደርጉት ይህ የድጋፍ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ወደ ስራ መግባቱን ገልጿል፡፡

ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ልዩ ልዩ የአደባባይ ኩነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ በትዕግስት፣በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በመደጋገፍ ላሳየው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

በሰልፉ ላይ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የፕሮግሙ ተዳሚዎች ተገንዝበው ለፍተሻ እንዲተባበሩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በመስቀል አደባባይ የሚደረገው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ የተወሰኑ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ፡፡ በዚህም መሰረት

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎፒያ አደባባይ
• ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ

• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
• ከቸርችር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ እና አገር አስተዳደር መብራት ወይሚ ኢሚግሬሽን

• ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

• ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

• ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ

• ከሳሪስ በጎተራ አጎና ሲኒማ እና አራተኛ ክፍለ ጦር
• ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
• ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት አካባቢ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በተጨማሪም በዋዜማው ከምሽት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ በሚከናወንበት እና ዝግ በሚሆኑ መንገዶች አካባቢ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቦ ህብረተሰቡ ጥቆማ ለመስጠት ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ሲፈልግ በ011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡