ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የምስክር መሰማት ሂደት የዕግድ ትዕዛዝ አውጥቶ ለ200ኛ ግዜ አስተጎግሎታል።


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

ዛሬ ሐምሌ 14 /2013 በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክር መሰማት ይጀምራል ተብሎ የተያዘውን ቀጠሮ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የዕግድ ትዕዛዝ አውጥቶ የምስክር መሰማቱን ሂደት ለ200 ኛ ግዜ አስተጎግሎታል። የእስክንድር ነጋ ባለቤት ጉዳዩን በተመለከተ በማሕበራዊ ድረገፅዋ ላይ እንዳለችው አንድ ግዜ ከመጋረጃ ጀርባ፣ ሌላ ግዜ በዝግ ችሎት በሚል ሰንካላ ምክንያት ከአንድ ዓመት በላይ ሲቀልድ የከረመው የፍትህ ተቁዋም ካለፈው ሥርዓት በባሰና በከፋ መልኩ የቁልቁለት መንገድ እየተጎዘ እንደሆነ ከእነ እስክንድር የክስ መዝገብ በላይ ማስረጃ የለም። ስትል አስፍራለች።

No photo description available.

May be an image of text