የምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪው ተገለው ተገኙ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

አቶ አይናድስ ሞላ ትናንት ማታ በግልገል በለስ ከተማ ተገድለው ተገኝተዋል – ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ምርጫ ክልል ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት አቶ አይናድስ ሞላ ደንበሩ በግልገል በለስ ከተማ ሞተው መገኘታቸውን ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳወቀ።

የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ ) በመተከል ዞን የሚወዳደር አባሉ እንደተገደለበት ገለፀ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን የሚወዳደረው ቦዴፓ የምርጫ ተወዳዳሪ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡

ፓርቲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳረጋገጠው በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ምርጫ ክልል ድርጅቱን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት አቶ አይናድስ ሞላ ድንበሩ መገደላቸውን አረጋግጧል፡፡

የቦሩ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዮሐንስ ተሰማ ለጣቢያችን እንደተናገሩት፤አቶ አይናድስ ሞላ ትናንት ማታ ነው በግልገል በለስ ከተማ ተገድለው የተገኙት።

“እጅግ በጣም አዛሳኝና ልብ ሰባሪ ክስተት ነው” የሚሉት አቶ ዮሀንስ የአሟሟቱ ሁኔታ ገና እየተጣራ ይገኛል ብለውናል።

ፓርቲው ለድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች፣ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛል ብለዋል የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በበርካታ የምርጫ ጣቢያዎች ባጋጠመው የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት ፤ምርጫው በድጋሚ እንዲደረግ መወሰኑ ይታወሳል፡፡