የሰሜን ወሎዎቹ ቆቦና ወልዲያ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የራያ ተፈናቃዮች እየተቀበሉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

በራያና አካባቢው የከፋ ሰብአዊ ጉዳት ሳይደርስ መንግሥትም ሆነ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲሰጡ ከዋጃና ጥሙጋ አካባቢ በጦርነቱ ምክንያት ሸሽተው የወጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አስታወቁ፡፡ የሰሜን ወሎዎቹ ቆቦና ወልዲያ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተፈናቃዮች እየተቀበሉ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ራሱን የትግራይ ኃይል ብሎ የሚጠራው አካል ኮረም፣ አላማጣ፣ ዋጃንና ጥሙጋን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሽዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው ከሰሜን ወሎዋ ቆቦ እስከ ደሴ በሚገኙ ሮቢት፣ ጎብዮ፣ አራዱም፣ ወልዲያና ሌሎች ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ወሎ በሚገኙት አዲስ ቅኝ፣ ራማ፣ ዞብል፤ ጎለሻ፣ ጀመዶ ማሪያምና ሌሎች የገጠር ከተሞች ተሰደው መሄዳቸውን አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ፡፡

ከዋጃ 15 ኪሎ ሜትር ምሽትን ተገን አድርገው በእግራቸው ተጉዘው ሐሙስ ሐምሌ 8/2013 ዓ.ም ቆቦ ከተማ መግባታቸውን አንድ የዕድሜ ባለጸጋ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በኩል ባስተላለፈው መልእክትም ሰራዊቱ ትዕዛዝ በሚሰጠው ጊዜ አስፈላጊውን ርምጃ ሊወስድ የሚያስችለው አቋም ላይ እንደሚገኝ መጥቀሱ ይታወሳል፡፡

Source – VOA Amharic : (ተፈናቃዮቹ የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)