የክልሉ ገዢ ህወሓት አማፅያን ወደፊት እየገፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሮች መቐለ ከተማን ለቀው ወጥተዋል


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ከደቂቃዎች በፊት በሰበር ዜና አማፅያን ወደፊት እየገፉ መምጣታቸውን ተከትሎ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሮች ለቀው ወጥተዋል ብሏል።እስካሁን እየወጡ ስላሉት መረጃዎች በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በኩል የተባለ ነገር የለም።

መቐለ ከተማ የቀድሞው የክልሉ ገዢ (ህወሓት) ታጣቂዎች መግባት ጀምረዋል የሚል መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ተሰምቷል። ነዋሪዎች የሞተር ሳይክሎች እና የመኪኖች ጥሩምባ እያሰሙ በመቐለ ጎዳናዎች ሲዘዋወሩ ታይተዋል። በመቐለ ርችት እየተተኮሰ መሆኑን እንዲሁም የትግራይ ክልል ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የከተማዋ ነዋሪዎች በጎዳናዎች ሲዘዋወሩ መታየታቸውን ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፌድራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ለቀው መውጣት መጀመራቸው ተሰምቷል። የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በኋላ ነው መቀዛቀዝ የጀመረው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከመቐለ ወደ ኲሃ አቅጣጫ ሲጓዙ መታየታቸውን ተሰምቷል።

የትግራይ ቴሌቭዥን ከዛሬ ጀምሮ ሥርጭቱ የተቋረጠ ሲሆን በትግራይ ክልል ሌሎች አካባቢዎች የቴሌኮም ግልጋሎት አይሰራም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከተማው የሚያደርገው ጉዞ ተቋርጧል። የክልሉ መንግሥት ዋና መቀመጫ የሆነችው መቐለ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር የሆነችው ሕዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ነበር።

ዘገባው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ከመቐለ) ነው።