6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሁለት ዙር እንደሚካሄድ ታውቋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሁለት ዙር እንዲደረግ ወሰነ::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በገጠሙ የህትመት ችግር፣ የጸጥታ ሁኔታና የዳታ ችግር ምክንያት ሀገራዊ ምርጫ በሁለት ዙር እንደሚካሄድ አስታውቋል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ÷ ክፍተት ከተገኘባቸው የምርጫ ክልሎች የጸጥታ ችግር አለባቸው ተብለው ሰኔ 14 ድምጽ ከማይሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር ድምጽ ይሰጥባቸዋል ብለዋል።

የቦርዱ የኦዲት ክፍል ባካሄደው ማጣራትም በ54 ምርጫ ክልሎች ላይ ክፍተት ተገኝቷል ተብሏል።

ምርጫው ከሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሌላ ሁለተኛው ዙር ምርጫም ጳጉሜ 1 እንደሚሆን ቦርዱ ወስኗል።

በተጨማሪም የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔም ከሁለተኛው ዙር ምርጫ ጋር ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ይደረጋል ተብሏል።

የሶማሌ ክልል ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ምርጫ ከማይደረግባቸው ቦታዎች አንዱ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በተሻሻለው የምርጫ 2013 ተመዝጋቢዎች ቁጥር ሪፖርት መሰረት አጠቃላይ የመራጮች ቁጥር 37,408,600 መድረሱን ያሳያል።

ከነዚህ ውስጥ 20,317,472 ወንዶች ሲሆኑ 17,091,128 ሴቶች ናቸው፡፡