የኤርትራ ጦር ሰራዊት በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች ይንቀሳቀሳል – በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW : በአቶ ዳውድ ኢብሳ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ.) ሰሞኑን በተደጋጋሚ በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ የኤርትራ ጦር ሰራዊት በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ ብሏል። በሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ጊዜያዊ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው መሰየማቸውን የሚገልጹት አቶ ለሚ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ጦሩ ቀደም ሲል በምዕራብ ኦሮሚያ አሁን ደግሞ በደቡብ ኦሮሚያ እየተንቀሳቀሰ ነው። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ መረጃውን መሰረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል።