የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በዛሬው መግለጫ ምን አለ ? (ሙሉ ቪዲዮ ከታች ያገኙታል)
የትግራይ መልሶ ማቋቃም ጤና ዘርፍ :
ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከተናገሩት ፦
– 52 ከመቶ ሆስፒታሎች መደበኛ ስራ ጀምረዋል።
– ባለፈው ሳምንት ከነበረው ሪፖርት አኳያ አሁን ላይ በክልሉ 55 ከመቶ ሆስፒታሎች እና 52 ከመቶ የጤና ማዕከላት ስራ ጀምረዋል።
– አገልግሎት በተጀመረባቸው የጤና ፋሲሊዎች 85 ከመቶ በላይ የጤና ባለሞያዎች የእለት ተለት ስራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
– በተቀሩ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰው ጉዳት ተገምግሟል። የፌዴራል መንግስት ባቀረበው በጀት በ14 ሆስፒታሎች እና 58 የጤና ማዕከላት አገልግሎት እንዲጀመር ይደረጋል።
– ለ40 የጤና ማዕከላት ኪትስ ተልኳል።
– የጤና ቁሳቁስ ከተላከባቸው አካባቢዎች መካከል መቀሌ፤ ኩይሃ ፤አቢ አዲ፤እና ሽሬ ይገኙበታል።
– የክልሉን የጤና አገልግሎት ለማስጀመር እስካሁን 310.8 ሚሊዮን በላይ የሚያወጣ መድሃኒት እና የህክምና መሳሪያ ወደ ክልሉ ተልኳል።
– የትግራይ ክልል ጤና መልሶ መቋቋም እንቅስቃሴ ምላሽ በማገዝ ሂደት የጤና ሚኒስቴርም ከአጋር አካላት ጋር በመሆን 215 በላይ ሚሊዮን ብር የሚገመት ገንዘብ ለክልሉ ተላልፏል።
– የጤና አገልግሎት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ተንቀሳቃሽ ቡድኖችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ተደራሽ የማድረግ ስራ በመከናወን ላይ ነው።
ሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ :
የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ከተናገሩት ፦
– ከ5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወይም 135 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ምግብ ሸቀጥ ተሰራጭቷል።
– በመጀመሪያ ዙር 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች ተጠቃሚ ተደርገዋል። በሁለተኛና በሶስተኛ ዙር 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
– 170 ሺህ 798 ሜትሪክ ቶን ምግብ ቀርቧል። ለዚህም ከ5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል።
– በ1ኛና በ2ኛ ዙር የተሰራጨው የሰብዓዊ ድጋፍ ወጪ 70 በመቶ በመንግስት እንዲሁም ቀሪው 30 በመቶ በአጋሮች የተሸፈነ ነው። በ3ኛ ዙር ድጋፍ መንግስትን ጨምሮ 6 አካላት ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።
– የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ ወርልድ ቪዥን፣ ኬር ኢንተርናሽናል፣ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት እና ፉድ ፎር ሀንግሪ በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ እየሰሩ ነው።
– መንግስት እየተደረገ ያለውን ድጋፍ እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ እንዲሳካ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው።
ምንጭ፦ ኢዜአ