የሠላሳ ዓመታት ግፍና በደላችን ዓለም እንዲያውቅልን እንፈልጋለን! – በወልቃይት ጠገዴ ሁመራ በሴቶች የሚመራ ሰልፍ ተካሄደ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


May be an image of 1 person, standing and skyሁመራ ከተማ ላይ ዛሬ በሴቶች የሚመራ ሰልፍ ተካሄደ። በትህነግ ዘመን ባሎቻቸውና ልጆቻቸው ታፍነው የጠፉባቸው፣ የተገደሉባቸው፣ የተሰቃዩባቸው፣ በቤተሰብ አስተዳዳሪዎች አለመኖር ምክንያት ብዙ የተሰቃዩ፣ እንዲሁም በወንበዴዎቹ የተደፈሩ የተሰቃዩ ሴቶች መሪነት ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ሴቶች ባለፉት 30 አመታት በርካታ ስቃዮችን አሳልፈዋል።በወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ከተማ በተካሄደው የሴቶች ሰልፍ የተላለፉ መልዕክቶች …………….
👉 የሠላሳ ዓመታት ግፍና በደላችን ዓለም እንዲያውቅልን እንፈልጋለን!
👉 ዓለም ያልሰማው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወልቃይት አማራ ላይ ተፈጽሟል!
👉 ወያኔ የፈጸመብን ግፍ ይታወቅልን!
👉 የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም፤
👉 የራሳችንም አሳልፈን አንሰጥም፤
👉ማንነታችን አማራ፤ ድንበራችን ተከዜ ነው!
May be an image of 6 people
👉ከትግራይ የሚመጣ ጥሩ ጎረቤት እንጅ፤ አስተዳደር ፈጽሞ አንቀበልም!
👉ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ብዙ ማይካድራዎችን አይተናል!
👉 ከትግራይ የሚመጣን አስተዳደር ከአሸባሪው ትህነግ ለይተን አናየውም!
👉 በማይካዳራ ጭፍጨፋ ቤተሰቦቼን አጥቻለሁ! ፍትህ እፈልጋለሁ!
👉 የአማራ ልዩ ኃይል ወልቃይት እንጅ ትግራይ ውስጥ የለም!
👉 የአጼ ቴዎድሮስ ልጆች ነነ ! ሉአላዊነትን ኑረንበት ነው የምናውቀው! አንበረከክም!
👉 ወልቃይትን አስከብረናል፤ ትግራይን አረጋጉ!!
👉 የአማራ የግፍ ጥግ ማሳያ ወልቃይት ነው!!
👉 በማንነታችንና በርስታችን አንደራደርም!!
👉 አሸባሪው ትሕነግ ይመለሳል ብላችሁ የምትጠባበቁ ከዳተኞች ተስፋችሁን ቁረጡ!!
👉 የአፍ መፍቻ ቋንቋችን አማርኛ ነው!
👉 ሕገ-መንግሥታዊ መብታችን ይከበር!
👉 የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ የፍትሕ ኢትዮጵያውያንም ጥያቄ ነው!
👉 ባሌን እና ሁለት ልጆቼን በወያኔ አጥቻለሁ! በሺህዎች የሚቆጠሩ የወልቃይት አማሮች እንደኔ ተበድለዋል!
👉አባት አልባ ልጆችን ማሳደግ መከራው የደረሰበት ያውቀዋል! እኔን የሆኑ ሺህ ሴቶች አሉ!
(አማራ ብልፅግና ገፅ ላይ የተወሰደ)
May be an image of one or more people, people standing, outdoors and crowd
May be an image of one or more people, people standing and outdoors
May be an image of 3 people, people standing and outdoors