ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የሞታቸው ምክንያት «ድንገተኛ» በሚል ከመገለፁ ባሻገር መንስዔው እስካሁን በትክክል አልታወቀም – አብን


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኮሚሽነሩን ሞት በተመለከተ በማኅበራዊ ድረገፆች እየተንሸራሸሩ የሚገኙ በርካታ ግምቶች ቢኖሩም የሞታቸው ምክንያት «ድንገተኛ» በሚል ከመገለፁ ባሻገር መንስዔው እስካሁን በትክክል አልታወቀም። ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከነበራቸው የሥራ ሥምሪትና ተያይዞ ከሚነሱት አወዛጋቢ የፖለቲካ ትንታኔዎች አኳያ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአማራ ሕዝብ ትክክለኛውን የኅልፈተ ሕይወታቸውን ምክንያት ማወቅ ይፈልጋል፣ የማወቅ መብትም አለው። – የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)  የኃዘን መግለጫ፤
*****
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እስከቅርብ ጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩት ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በዛሬው ዕለት በድንገት ሕይወታቸው ማለፋን ሰምተናል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በወንድማችን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅና መሪር ኃዘን ይገልፃል።

የኮሚሽነሩን ሞት በተመለከተ በማኅበራዊ ድረገፆች እየተንሸራሸሩ የሚገኙ በርካታ ግምቶች ቢኖሩም የሞታቸው ምክንያት «ድንገተኛ» በሚል ከመገለፁ ባሻገር መንስዔው እስካሁን በትክክል አልታወቀም። ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከነበራቸው የሥራ ሥምሪትና ተያይዞ ከሚነሱት አወዛጋቢ የፖለቲካ ትንታኔዎች አኳያ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአማራ ሕዝብ ትክክለኛውን የኅልፈተ ሕይወታቸውን ምክንያት ማወቅ ይፈልጋል፣ የማወቅ መብትም አለው። ስለሆነም የሚመለከተው የመንግስት አካል የኮሚሽነሩን ኅልፈት ትክክለኛ ምክንያት በአስቸኳይ ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ አብን ያሳስባል።

ትክክለኛ ምክንያቱ ተጣርቶ ይፋ እስኪደረግ ድረስ ሕዝባችን የተለያዩ ፍላጎቶች ባሏቸው አካላት ከሚሰነዘሩ የተሳሳቱና አፍራሽ ሐሳቦች በተለይም መረጃ ከማስተላለፍ፣ ከመዘገብ ወይም ከማቅረብ ያለፈ ዓላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ አካላት ከሚፈጥሯቸው አወዛጋቢ የሴራ ትንታኔዎች እንዲቆጠብና በጥንቃቄ እንዲመለከታቸው መልእክታችንን ማስተላለፍ እንወዳለን።

አብን በኮሚሽነር አበረ አዳሙ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን መሪር ኃዘን እየገለጸ ለኮሚሽነር አበረ አዳሙ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የአማራ ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር!