አውሮፓ ህብረት የምርጫ ውጤት ከምርጫ ቦርድ ቀድሜ ይፋ ላድርግ የሚሉት ፍላጎቶቹ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ስለሚፈታተን እና ተቀባይነት የሌለው ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አምባሳደር ዲና ስለአውሮፓ ህብረት :

የአውሮፓ ህብረት በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ታዛቢዎችን አልክም ማለቱ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን የሚጻረር አካሄድን አልቀበልም በማለቷ ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ህብረቱ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያ ውጪ የራሴን ይዤ ልግባ ማለቱን አንስተው ለመግለጫው አንዱ ምክንያት ይህ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከምርጫው ጋር በተገናኘ የምርጫ ቦርድን ተግባር እንዲሁም ኃላፊነት የሚጸረር ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበተል ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ የምርጫ ውጤት ከምርጫ ቦርድ ቀድሜ ይፋ ላድርግ የሚሉት ፍላጎቶቹ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ስለሚፈታተን እና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ነው ህብረቱ ለስድስተኛው የሀገራዊ ምርጫ ታዛቢዎችን አልክም ያለው ብለዋል። ~ ኤፍቢሲ