የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን የካይሮ ስብሰባ መሰረዛቸው በግብፆች ዘንድ ድንጋጤን ፈጥሯል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አብደላህ ሐምዶክ የግድቡን ጨዋታ በመቀየር ላይ
° የዓባይ ልጅ °

“ዋስትና የምናገኘው ከካይሮ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ነው” ብለዋል። ሳዲቅ አል-ማህዲ ከካይሮ ያላትን ትስስርም ከልክለዋል።

May be an image of 3 people and textአል-አረቢያ የግብፅ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሰፊ ዘገባ አስነብቧል። ምንጮቹ እንዳሉት ግብፅ የሱዳንን አቋም “አደገኛ” ሲሉ ገልፀውታል።
በሱዳንና ግብፅ መካከል የተፈጠረው የአቋም ልዩነት የሱዳን ውጭ ጉዳይ ምኒስትሯ ማርያም አል-ማህዲ ከግብፁ አቻ ሳሚህ ሹክሪ በካይሮ ሊያካሂዱት የታቀደው ስብሰባ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከግብፁ ውጭ ጉዳይ ሳሜህ ሹኩሪ ጋር ለመምከር የሱዳኗ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማሪያም ሳዲቅ አል-ማህዲ ወደ ካይሮ ለመጓዝ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩ ስብሰባው በሐምዶክና እሳቸው ባደራጁት የባለ ስልጣናት ጥምረት መሰረዙ ነው ምንጮቹ ለአል-አረቢ የጠቀሱት፡፡ የሱዳን መስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ መካከል በህዳሴ ግድቡ ውጥረት ዙሪያ የማያግባቡ አካሄዶች እንደነበሯቸውም አል-አረቢ ጠቁሟል። ሐምዶክ የግድቡን አለመግባባት የኃይል ካርድ መፍትሄ አይደለም የሚል አቋም ነው ያላቸው ብሏል ዘገባው።

° የቢን ዛይድ ቀይ መስመር በግብፅ ላይ
የግብፅ ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንዳሉት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በግብፅ መንገድ ሲጎዝ የነበረውን የሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት ላይ ጫና ለማሳደር በሲቪሉ ክንፍ በኩል ተከታታይ ግፊት እያደረጉ ናቸው።
ካርቱም በተፈጠረው ቀውስ ዙሪያ በካይሮ ፍላጎት ተጠልፋ እንዳትወድቅ የራሷ አቋም እንድትጓዝ አሰየሰሩ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ከግብፅ አካሄድ በተለየ ሁኔታ ኢትዮጵያ የሱዳንን ስጋቶች ከግምት እንደምታስገባና ሁለተኛው ሙሊት ከመጀመሩ በፊት ሙሉ የቴክኒክ ቅንጅትና በአተገባበሩ ላይም ከአዲስ አበባ እውነተኛ ዋስትናዎች እንዳሉ ለተለያዩ የሱዳን ባለስልጣናት እያስገነዘቡ ናቸው ተብሏል፡፡

በቅርቡ ካይሮን የጎበኙት የአቡዳቢ መሪ ቢን ዛይድ የህዳሴ ግድቡን ቀውስ ለመፍታት ባቀረቡ አዲስ የመፍትሔ ማዕቀፍ ውስጥ ለአል ሲሲ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሏል። ወደ ግጭት እንዳይገባ አማራጭ የሰጡት ቢን ዛይድ ለግብፅ የሚያቀርቡትን ገንዘብ ለማዘግየት ወስነዋል። አል ሲሲ ከአቡ ዳቢ እየጠበቁት የነበረው የሚያዝያ፣ ግንቦትና ሰኔ ወር 2.5 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ገንዘብ ትዕዛዙን ተፈፃሚ እስሚያደርጉ ድረስ እንደማሰጣቸው ተነግሯቸዋል።

“ቢን ዛይድ በካይሮ” በሚል በሳምንቱ ባሰፈርኩት መረጃ ውስጥ ‘ሙሐመድ ቢን ዛይድ በካይሮ ጉብኝታቸው ከያዟቸው አጀንዳዎች ውስጥ በግድቡ አለመግባባት ዙሪያ የሱዳን ጦር ባለስልጣናት ከካይሮ የፈጠሩትን ጠብ አጫሪ ቅንጅት መበጠስ አንዱ ነው” የሚለውን ጉዳይ እዚህ ላይ ማስታወስ ያስፈልጋል። ከሰሞኑ እየታየ ያለው የሱዳን አካሄድም ያንኑ ተከትሎ የተከሰተ መሆኑ ነው የተነገረው።

አል-አረቢ ዋቢዎች ጠቅሶ ባስነበበው ሌላ መረጃም ቢን ዛይድ የፖለቲካ አማካሪያቸው ባለፈው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋር እንዲወያዩ በድብቅ ልከዋቸዋል። የኤሚሬት ጥረት አንድም ግብፅ የምታራምደው አካሄድ ወደ ግጭት አምርቶ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንቨስትመንቷ እክል እንዳይገጥመው ያለመ ነው(የተባበሩት አረብ ኤምሬት በሦስቱም አገሮች ሰፋፊ ኢንበስትመንት እንዳላት ዘገባው አስታውሷል)። አል-አረቢ ከምንጮቹ ያገኘውን ተጨማሪ መረጃ ጠቅሶ “የቢን-ዛይድ አማካሪን የአዲስ አበባ ጉብኝት በተመለከተ ኤሚሬትስ ምንም ነገር ሳታሳውቃት እንደነበር የተረዳችው ካይሮ ሁሉም ካለፈ በኋላ መሆኑ ያስደነገጣት ሆኗል” ብሏል።

የግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሊት ሁለት ወራት በቀሩት በዚህ ጊዜ አብደላህ ሐምዶክ ከሽግግር ባለ ስልጣናቱ ጫና የተላቀቀ ጠንካራ አመራር በመስጠት ላይ ነው የሚገኙት።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ