የኦሮሞ አክራሪ ብሄረተኞችን መታገል እንጂ ማባባል አይሰራም #ግርማ_ካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ታማኝ ለጃዋር ጥሪ አቅርቧል። ጃዋር ግን ይሰማል ብዬ አላስብም። እነ ጃዋርን መለማመጡ ቆሞ፣ ኢትዮጵያን የሚል የኦሮሞ ማህበረሰብን የማቀፍ ስራ መሰራት ነው ያለበት ባይ ነኝ” ብዬ ነበር። የኦሮሞ ወጣቶችን አጋዚ ሲጨርሳቸው፣ የኦሮሞ ተቃውሞ ወደ ሌሎች ቦታዎችም መሸጋገር አለበት፤ ሌላውን ባቀፈ መልኩ እናስፋው በሚል ብዙ ጥያቄ ሲቀርብለት ነበር። እነ ኦባንግ ሜቶ ያሉ አክቲቪስቶች ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፣ እነ ጃዋርን ለማግባባትና ለማሳመን። ሆኖም አልተሳካም።

አሁን ጃዋር እኛ ነን ለዉጥ ያመጣነው ብሎ ቢፎክርም፣ የነጃዋር ንቅናቄ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ተጨፍልቆ እንደነበረ  ሁሉም የሚያወቀው ነው። እነ አቶ ለማ ኦሮሞ ለብቻው በመቆሙ እንደጎዳው እንጂ እንዳልጠቀመው ተረድተው፣ የኦሮሞ ጥያቄ ልክ እንደሌላው ማህበረሰብ የፍትህ፣ የሰላም፣ የዲሞክራሲን፣ የልማት ጥያቄ መሆኑን አውቀው፣ ኢትዮጵያ ብለው ተነሱ። ከነ ገዱ ጋር አብረው በመስራት፣ በመደመር ነው ለዉጥ እንዲመጣ ያደረጉት። እነ ገዱ ባይኖሩ ኖሮ ፣ እነ ገዱ ደግሞ በባእዴን ውስጥ አይለው እንዲወጡ የአማራ ክልል ወጣቶች ግፊት ባያደረጉ ኖሮ፣ አቶ ለማና ዶ/ር አብይ ይሀን ጊዜ ወህኒ ነበሩ። ሽፈራው ሽጉጤ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆን ነበር።

ለታማኝ ጃዋር የመለሰው መልስ ጥጋብ የተሞላበት መልስ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነት ንቀት እንዳለው በግልጽ፡ያሳየበት ነው። አሁንም የኦሮሞ ብሄረተኞን ለሚለማመጡና ለሚያባብሉ ትልቅ ትምህርት የሰጠ ነው።

ጃዋር እንደሚያወራውና እንደሚፎክረው በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ በሁሉም ቦታ ድጋፍ የለውም። የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ሁሉም እንደ ጃዋር እንደሚያስብ አድርጎ የኦሮሞን ክልል ለነ ጃዋር ብቻ አሳልፎ መተው ትልቅ ስህተት ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ማህበረሰብን አሳንሶ ማየት ነው። በኦሮሞ ክልል በተደራጀ መልኩ ሕዝቡን ማንቀሳቀስና ማስተማር በጣም አስፈላጊ ነው።የአንድነት ሃይል ነን የምንል ሰዎች እንደውም ጉልበትና ጊዜ ማጥፋት ያለብን በኦሮሞ ክልል ነው። እነርሱ ስለሚጮኹ የሌላው ድምጽ አይሰማም እንጂ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የኦሮሞ ልጅ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ነው።

አንድ ጦማሪ “ከወያኔ ወደ ቄርያኔ” ብሎ የነጃዋር የቄሮ ቡድንን ከወያኔዎች ጋር ለማመሳሰል ሞክሯል። ትክክል ነው። ከዚህ በኋላ ትኩረቱን ትግሉ መሆን ያለበት የነጃዋርን ዘረኛ፣ ጠባብ ፖለቲካን ማሸነፍ ነው። ይሄን ለማድረግ ስትራቲጂ አስፈላጊ ነው።

፩. በቅድሚያ በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ሌሎች ማህበረሰባትን፣ በኦሮሞ ክልል ኢትዮጵያዊነት ስር የሰደደባቸው የኦሮሞ ማህበረሰባት አባላትን በሚገባ ማደራጀት ያስፈልጋል።፡በተለይም እንደ ሸዋ፣ ጂማና ኢልሊባቡር ያሉ ቦታዎች። እንደዉም ሸዋ አዲስ አበባን አካቶ የራሱ መስተዳደር እንዲሆን ግፊት ማድረጉ በጣም ወሳኝ ነው።፡ጂማና አካባቢዋም እንደዚሁ።

፪. አክራሪነትና የኦነግ አስተሳሰብ ስር በሰደደባቸው፣ የጃዋር ደጋፊዎች በበዙባት እንደ አርሲ፣ ባሌና ሃረርጌ ባሉ አካባቢዎች ፣ አክራሪነት በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በኢንቨርስተመንት ወደ ኋላ እንዳቀስቀራቸው ፣ እንደጎዳቸው በማሳየት ያለዉን እዉነታ እንዲረዱ ማስተማር፣ በሌሎች ክልሎች ከተሞችና እነርሱ በሚኖሩባት አካባቢ ያለውን ልዩነት ማሳየት አስፈላጊ ነው። ዕነርሱ አክራሪነት፣ መለየትን በመረጡ ጊዜ ፣ መንደራቸው፣ ከተሞቻቸው ለንግድ፣ ለኢንቨርስተንት፣ ለመዝናናት ..የሚመጣ አይኖርምና..፡፡

በተለይም በርካታ የኦሮሞ ልጆች አሉ፣ በጃዋር ቄሮዎች intimidate እየሆኑ ወጥተው መናገር የሚፈሩ። ለነዚህ ወገኖች ዝምታቸውን ስብረው እንዲወጡ አበረታታቸዋለሁ። እነ ጃዋር ያደራጇቸውን ወጣቶች ይዘው የሕዝቡ ጥቅም እንዲጎዱ ሊፈቀድላቸው አይገባም። ለኦሮሞ ማህበረሰብ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ተለይቶ፣ እየተፈራ፣ እየተጠላ መኖሩ ጎድቶታል፤ ይጎዳዋልም። እነ አቶ ለማ እየገነቡት ያለውን ድልድይ እነ ጃዋር እንዲያፈርሱ የኦሮሞ ልጆች መፍቀድ የለባቸውም።

ይሄ ብዬ ለተቀረነው፣ ደግሜ እላለሁ፣ አክራሪ የኦሮሞ ብሄrእተኞች፣ እነ ጃዋር መለማመጥና ማባባል አያስፈለግም። የተቀናጀ ትግሉ በነርሱ ላይ መደረግ መጀመር አለበት። የወያኔን ቦታ ይዘው፣ አሁን ለአገራችን፣ ለደህንነታች፣ ለሕልዉናችና ለሰላማችን ጠንቅ የሆኑት ቄሪያኖች ናቸው።