የአሜሪካ ፕሬዝደንት ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ጃክ ሰሊቫን የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ፀጥታን ያናጋዉ ግጭት እና ጥቃት እንዳሳሰባቸዉ አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ጃክ ሰሊቫን የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ፀጥታን ያናጋዉ ግጭት እና ጥቃት እንዳሳሰባቸዉ አስታውቀዋል።

ዋይት ሐዉስ፥ የፀጥታ አማካሪዉ ከም/ጠቅላይ ሚንስትር እና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ትናንት በስልክ ባደረጉት ዉይይት በተለይ ትግራይ ክልል ዉስጥ የሚደረገዉ ግጭት እንዳሳሰባቸዉ አስታዉቀዋል።

ሮይተርስ ዋይት ሐዉስን ዋቢ እንድርጎ እንደዘገበው፥ 2ቱ ባለስልጣናት ትግራይ ዉስጥ ለተቸገረዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ስለሚቀርብበት ፣ ግጭቱ ስለሚረግብበት ፣ የዉጪ ወታደሮች ስለሚወጡበትና የደረሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደል በገለልተኛ ወገን ስለሚጣራበት ሁኔታ ተነጋግረዋል።

ከትግራይ ክልል በተጨማሪም በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉት የጎሳ ግጭቶችና ጥቃቶች በዉይይቱ መነሳቱ ተጠቅሷል።

በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የገጠመችዉን ዉዝግብ ለማስወገድ የሚደረገዉ አካባቢያዊ ዉይይት መቀጠል እንዳለበት መወያየታቸውን ኃይት ሐውስ አሳውቋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በይፋዊ የማህበራዊ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በትግራይ ያለው ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑንም በስልክ ውይይቱ ወቅት እንዳብራሩ ገልፀዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ታዛቢዎች በፍትሃዊነት እና በገለልተኝነት እንዲያገለግሉ በማሰብ በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ድርድር ቁልፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈታ እንዳረጋገጡላቸው አስፍረዋል።

Source – Deutsche Welle , Reuters, www.whitehouse.gov