የረመዳን ጾምን በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የረመዳን ጾምን በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስተናገሩ፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ በሰጡት መግለጫ ወሩን በመተሳሰብ፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል ብለዋል፡፡
ከወንጀል እና ከበደል በመቆጠብም ወደ አምላክ መቅረብ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል፡፡
በመግለጫው በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የዜጎችን ሞትና መፈናቀል አውግዘው፥ መንግስትና ህግ አስከባሪ አካላት የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶች ህዝቡን ማስተማር ይገባቸዋል ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ፥ ለአንድነትና ለሰላም ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡