በእነ አቶ ስብሃት ነጋ ላይ ሊሰማ የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ታገደ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በእነ ስብሃት ነጋ ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሊያሰማው የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ለጊዜው ታገደ።

ምስክርነቱ የታገደው የተከሳሽ ጠበቆች በምስክር አሰማም ሂደቱ ላይ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለታቸው ነው።

ዐቃቤ ህግ የአቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ የ42 ተጠርጣሪዎችን የጊዜ ቀጠሮ እየተመለከተ ላለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ከዚህ ቀደም ባቀረበው አቤቱታ፤ የቅድመ ምርመራ የምስክርነት ሂደቱ በዝግ ችሎት እና በስውር እንዲሆን ጥያቄ አቅርቦ ነበር። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ይህንን አቤቱታ ተቃውመው ለችሎት አቤት ቢሉም መቃወሚያቸው ውድቅ ተደርጓል።

ጠበቆቹ ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ መጠየቃቸውን ተከትሎ ፤ የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የቅድመ ምርመራ የምስክር መስማት ሂደቱ ታግዶ እንዲቆይ በዛሬው ውሎው ወስኗል።

ችሎቱ “የይግባኝ ክርክሩ መልስ እስኪያገኝ ድረስ መዝገቡ ተዘግቶ ይቆያል” ሲል በዛሬው ውሎው ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ዛሬ መጋቢት 29 በነበረው ችሎት ፤ አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ 39 ተጠርጣሪዎች በአካል ተገኝተው ተከታትለዋል። በዛሬው ችሎት ሰሎሞን ኪዳኔ እና ብርሃነ ጸጋዬ በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘግቧል።