የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙኃን ማድረግ ሊጀምሩ ነው – የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰዓትና የጋዜጦች አምድ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ከነገ ጀምሮ በመገናኛ ብዙኃን ማድረግ እንደሚችሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ነፃ የአየር ሰዓት እና የጋዜጣ አምድ እጣ ድልድል መርሐ-ግብር እየተከናወነ ነው።

ድልድሉ 25 በመቶ ለፓርቲዎች በእኩል ክፍፍል የሚሰጥ ሲሆን፣ በስራ ላይ ባሉ የፌዴራልና የክልል ምክር ቤት ወንበር 5 በመቶ፣ በእጩ ብዛት 40 በመቶ፣ በሴት እጩ 20 በመቶ፣ በአካል ጉዳተኛ እጩ ብዛት 10 በመቶ መሰረት በማድረግ ድልድል ተደርጓል ተብሏል።

ድልድሉ ለ46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ52 መገናኛ ብዙሃን ማለትም በ21 ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በ23 ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና በ8 ጋዜጦች የሚከናወን ነው ተብሏል።

በሬዲዮ 620 ሰዓታት፣ በቴሌቪዥን 425 ሰዓታት እና በጋዜጣ በ625 አምዶች የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የእጣ ድልድሉ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ብሮድካስት ባለሥልጣን በጋራ በተዘጋጀ መድረክ እየተከናወነ ሲሆን በዚህም ፓርቲዎች በተደለደለላቸው እጣ መሠረት ከመጋቢት 30 እስከ ግንቦት 23 በመገናኛ ብዙኃን ነፃ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰዓትና የጋዜጦች አምድ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የአየር ሰአትና የጋዜጦች አምድ ድልድል ስርዓት አስተዳደርን በማስመልከት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በጋር መግልጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሃመድ ኢድሪስ በመግለጫቸው እንዳሉት፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብዙሃን መገናኛዎች የሚኖራቸውን ነፃ የአየር ሰአትና የጋዜጦች አምድ በሚከተለው መንገድ ገልጸዋል።

1) ለራዲዮኖች 625 ሰዓታት
2) ለቴሌቪዥኖች 425 ሰዓታት
3) ለጋዜጠኞች ደግሞ 615 አምዶች መደልደላቸውን አስታውቀዋል።

የሰዓታት ምደባው የተወዳዳሪ እጩዎችን ብዛት፣ የሴት ተወዳዳሪዎችንና ተወዳዳሪ የአካል ጉዳተኞችን ባገናዘበ መልኩ መውጣቱን ተናግረዋል።

በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢው አቶ ውብሸት አየለ እንዳሉት የአሁኑ ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጦች አምድ አስከዛሬ ከነበሩት ምርጫዎች የቅስቀሳ ቆይታዎች በእጥፍ ጭማሪ እንዳለው አመላክተዋል።

ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን ገለልተኛ በመሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ቢሆኑ በሚሰጣቸው ሰአታት በህጋዊና በዲሞክራሲዊ አግባብ እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

እያንዳንዱ ፓርቲ በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚሰጠውን ነፃ የቅስቀሳ ጊዜ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው ሶፍትዌር በመግባት ማግኘት እንደሚችሉ በመግለጫው ተመላክቷል።

እንዲሁም ከነገ መጋቢት 30 ጀምሮ እስከ ግንቦት 23/2013 ዓ.ም ድረስ ነፃ የቅስቀሳ ጊዜው የሚያበቃ እንደሆነና ከነገ ጀምሮ ፓርቲዎች ቅስቀሳቸውን መጀመር እንደሚችሉም ተገልጿል።