ትግራይ ውስጥ በአውቶብስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 6 ተማሪዎች ተገደሉ

ተመራቂ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አሳፍሮ ከመቀለ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ በነበረ አውቶብስ ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ ስድስቱ ሲገደሉ ሌሎች መቁሰላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኖች የሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ ገለፁ። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የካቲት 11/2013 ዓ.ም አርባ አንድ ወጣት ሴቶችና ወንዶችን አሳፍሮ ይጓዝ በነበረው አውቶቡስ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው አዲ መ…