እጩዎቻችን እና አባላቶቻችን ታስረዋል፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽሕፈት ቤቶችን ተዘግተዋል፤ በዚህ ሁኔታ በምርጫው እንዳንሳተፍ እየተገፋን ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የ2013 ግንቦት ወር የምርጫ ዝግጅት

እንወያይ

DW : በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የኮሮና ተሐዋሲ ወረርሽኝ ያደናቀፈውን ምርጫ ዘንድሮ ለማካሄድ ሦስት ወራት ገደማ ቀርተዋል። በምርጫው የሚሳተፉ ጥቂት የማይባሉ ፓርቲዎች የሚለዩበትን አርማ መርጠው፣ እጩዎችንም እያስመዝገቡ ለምርጫ ቅስቀሳዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። በአንጻሩ እጩዎቻችን እና አባላቶቻችን ታስረዋል፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽሕፈት ቤቶችን ተዘግተዋል፤ በዚህ ሁኔታ በምርጫው እንዳንሳተፍ እየተገፋን ነው የሚሉም አሉ። ገዢው ፓርቲ በበኩሉ ከዚህ ቀደሙ የተሻለና የተለየ ምርጫ እንዲካሄድ የበኩሉን እያደረገ መሆኑን ይናገራል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።