ቀጣዩ 5 ዓመታት የብሔራዊ መግባባት ውይይት የሚደረግበትና ሕገ መንግሥት የሚሻሻልበት መሆን አለበት – ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አል ዐይን – ቀጣዩ 5 ዓመታት የብሔራዊ መግባባት ውይይት የሚደረግበትና ሕገ መንግሥት የሚሻሻልበት መሆን እንዳለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ፕሮፌሰር በየነ አንድ መንግስት አሸንፎ መንግሥት ማቋቋም ቢችል በዚህ አገር የዴሞክራሲ ሽግግሩ ተጠናቋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸው ከዚህ ምርጫ በኋላ ያሉት አምስት ዓመታት የብሔራዊ አንድነት መንግሥት የሚቋቋምበት መሆን እንዳለበት አንስተዋል፡፡

አሸናፊው ፓርቲ ሌሎች ፓርቲዎችንም በመጋበዝ ለአገር አንድነት ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ አምስት ዓመታት ብሔራዊ አንድነት ወይም ብሔራዊ መግባባት በሰፊው ውይይት ሊካሄድበት፤ የፖለቲካ ምኅዳሩም ሊደላደል፤ ሕገ መንግሥቱም ሊሻሻል የሚችልበት እንዲሆን ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

የሕገ መንግሥት መሻሻያም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሊካሄድ እንደሚገባ ፕሮፌሰር በየነ ያነሳሉ፡፡ ልክ እርሳቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሆነው የመንግሥት የሥራ ኀላፊ እንደሆኑት ሁሉ የሌሎች ፓርቲዎች አባላትነ አመራችም ወደ መንግሥት ኀላፊነት መጥተው አገር የሚገለግሉበት ዕድል እንዲፈጠርም ጠይቀዋል፡፡ መተማመን ያለበት ሁኔታ ለመፍጠር አሸናፊው ፓርቲ ከሌሎችም ፓርቲዎች ጋር ተደባልቆ ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል።