" /> በራያ የኮረም ወረዳ የሕወሓት የጸጥታ ሃላፊ በአደባባይ ሰው ገደለ። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በራያ የኮረም ወረዳ የሕወሓት የጸጥታ ሃላፊ በአደባባይ ሰው ገደለ።

Photo File የመከላከያ ሰራዊቱ በራያ 

ትላንት ማታ 3 ሰአት በራያ የኮረም ወረዳ የሕወሓት የጸጥታ ሃላፊ የሆነው ስዩም የተባለው ሰው በማን አለብኝነት ሰላማዊ የሆነውን ዝናቡ አሜሪካ (አሜሪካ የቅጽል ስም ነው) የተባለው ሰርቶ አዳሪ ሚስኪን ግለሰብን አደባባይ ላይ በጥይት ደብድቦ ገድሎ እስከ ዛሬ ጧት 3 ሰአት ድረስ በኮረም ይዘዋወር ነበር፡፡

ከዚህም በላይ የወረዳው ፖሊስ አስከሬኑ ወደ መቀሌ ሄዶ እንዳይመረመር የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠረ ሳይፈቅድ ቀርቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በኮረም ከተማ ህዝብና በታጠቁ የስርአቱ ሃይሎች በተፈጠረው አለመጋባባት ወደ ድንጋይ ውርወራና ተኩስ መገባቱ ተሰምቷል ፡፡

Agezew Hidaru


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV