አዲስ አበባ እንገባለን ባሉት መሠረት አዲስ አበባ ገብተዋል0


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

አዲስ አበባ እንገባለን ባሉት መሠረት አዲስ አበባ ገብተዋል


ሁለት የሕወሓት ጄኔራሎችና 13 መኮንኖች ሲገደሉ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አባይ ወልዱን ጨምሮ የሕወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ አዲስ አበባ እንገባለን ባሉት መሠረት አዲስ አበባ ገብተዋል

በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-

1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረ

2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ

3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች

4ኛ – ሁለት መስመራዊ መኮንኖች

5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀለ ናቸው።

በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ገልፀዋል።

እነዚህም

1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ

2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ

3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ

4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ

5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ

6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ

7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ መሆናቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ለኢዜአ ገልፀዋል።