ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በሻሸመኔ አሰቃቂውን ግድያ የፈጸሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል

(ኢሳት) – በሻሸመኔ ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ እንደተናገሩት በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት እጃቸው ያለበትን አካላት በመያዝ ለፍርድ ለማቅረብ ሂደቱ ተጀምሯል።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድንን ለመቀበል በአስርሺዎች የሚቆጠሩ የሻሸመኔና አካባቢዋ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉም ታውቋል።

ፖሊስ ከተማዋን ለማረጋጋት እየሰራሁ ነው ብሏል።

በሻሸመኔ በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመውን ግድያ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል።

የሻሸመኔው አሰቃቂ ግድያ ብዙዎችን አስደንግጧል።

አንድን ግለሰብ በድብደባ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ቁልቁል ተሰቅሎ የሚታይበት ፎቶግራፍ በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች በስፋት ተሰራጭቷል።

ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን በማውገዝ የተቃውሞ መልዕክቶችን በየመድረኩ አሰምተዋል።

VOA

ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የልዑካን ቡድን አባላት አቀባበል የወጣው የሻሸመኔ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪ በተሰሳሳተ መረጃ በተፈጠረ ግርግር አራት ሰዎች ተረጋግጠው መሞታቸንም ለማወቅ ተችሏል።

ቦምብ ይዟል ብሚል ያልተጣራ መረጃ ተደብድቦ የተገደለው ወጣት ከተሰቀለም በኋላ በመኪና ለመጎተት የተደረገው እንቅስቃሴ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

ጉዳዩ ከውግዘት ባለፈ ድርጊቱን በፈጸሙ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠይቋል።

በዛሬው ዕለት ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔት ወርክ መግለጫ የሰጡት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አሰቃቂውን ግድያ የፈጸሙት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

በሻሸመኔ ከተማ ቦምብ ተገኝቷል በሚል የተፈጠረው ግርግር የሰው ህይወት ማጥፋቱንም በመግለጽ መረጃ ትክክል አልነበረም ብለዋል።

ፖሊስ እስከአሁን ባደረገው ማጣራት ቦምብም ይሁን ከቦምብ ጋር የሚመሳሰል ምንም ዓይነት ነገር እንዳልተገኘ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ለኦቢኤን ገልጸዋል።

ሻሸመኔ ከገባችበት አለመረጋጋት እየወጣች ሰላም እየሰፈነ ያሉት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ዓለማየሁ እጅጉ አጠቃላይ የተፈጠረው ሁኔታ በተመለከተ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን መናገራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ ፈጽመው የሰቀሉት አካላት በቁጥጥር ስር መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ምርመራው እንድተጠናቀቀ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ጠቁመዋል።

OPINION by Mesfin Feyisa