መሰረዝ የነበረበት ፓርቲ ቢኖር በቁጥር 1 ደረጃ ብልፅግና ነው። – አቶ ልደቱ አያሌው


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

ኢዴፓ በምርጫ ቦርድ የመስራች ፊርማ አሟሉ ከተባልነው10ሺህ ፊርማ በላይ 17ሺህ አካባቢ አስፈርመን ከሚጠበቅብን 10 ሺህ ፊርማ በተጨማሪ መጠባበቂያ ከ3ሺና ከ4ሺ ፊርማ በላይ አቅርበን ነበር

ነገርግን ምርጫ ቦርድ ማጣራት ባለካሄደበት፥ለኢዴፓ ባለማከረበት፥ ማስጠንቀቂያ ባልሰጠበት ሁኔታ በብጣሽ ወረቀት 21አመት በሰላማዊ ትግል የቆየን ፓርቲ ሰረዝኩ ብሏል።

በወጣው መስፈርት መሰረት መሰረዝ ከነበረበት በቁጥር አንድ ደረጃ የሚሰረዘው ብልፅግና ነበር በምርጫ ቦርድ መስፈርት መሰረት አንዱንም አያሟላም፦
1ጠቅላላ ጉባኤ አላካሄደም
2ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈፃሚ በጉባኤ አላስመረጠም
3ፕሮግራምና ደንቡን በጉባኤ አላፀደቀም
4 የፓርቲውን መሪ በጉባኤ አላስመረጠም
ስለዚህ መስፈርት ባለሟሟላት መሰረዝ የነበረበት ፓርቲ ቢኖር በቁጥር 1 ደረጃ ብልፅግና ነው።
አቶ ልደቱ አያሌው