ምሽት ላይ ማንነታቸውን የማናውቃቸው ሰዎች አይተውን ይሄዳሉ እዚህም መጥተው እንዳይጨርሱን ስጋት ላይ ነን – የመተከል ተፈናቃዮች በቻግኒ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

የመተከል ተፈናቃዮች አሁንም የታጣቂዎች ጥቃት ስጋት አንዳለባቸው ተናገሩ።

ከመተከል ተፈናቅለው ቻግኒ የሚገኙ ተፈናቃዮች ምሽት ላይ ማንነታቸውን የማናውቃቸው ሰዎች አይተውን ይሄዳሉ እዚህም መጥተው እንዳይጨርሱን ስጋት ላይ ነን ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ባረጋገጥነው መሰረትም 22 ሺህ የሚደርሱት ተፈናቃዮቹ እየተጠበቁ ያሉት በጥቂት ሚሊሺያዎች ብቻ ነው፡፡

ካለው ስጋት አንጻር መንግስት መከላከያ ሰራዊት አልያም ፌደራል ፖሊስ ያምጣልን ሲሉ ተፈናቃዮቹ ጠይቀዋል፡፡

የጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብርሀኑ መኮንን በበኩላቸው ተፈናቃዮቹ ያሉበት አካባቢ ጫካ ያለበት በመሆኑ ያለባቸውን ስጋት እኛንም አሳስቦናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተፈናቃይ መስለው ተቀላቅለው የመጡ ሰዎችንም ይዘናል ሲሉ አክለዋል፡፡

ቻግኒ አካባቢ 22 ሺህ ተፈናቃይ ያለ ሲሆን እስካሁን ድረስ በአዊ ዞን አጠቃላይ 47 ሺህ 996 ተፈናቃይ እንዳለ አቶ ብርሀኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡