የግብፅና የሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለኢትዮጵያ ኪሳራ(ስጋት) አይደለም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የዉጭ ጉዳይ ሚ/ር መግለጫ

DW : በስድስት የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የተደረገዉና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራዉ የልዑክ ቡድን የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድን መልክት ያደረሰ፤ ብሎም በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለዉን ሕግ የማስከበር ተግባር ለጎረቤት ሃገራት ያስገነዘበ ነበር ተብሏል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እያከናወነችው ላለው ሕግ የማስከበር ተግባር ለጎረቤት ሀገራቱ ጥሩ ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ሀገራቱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን፣ ጣልቃ እንደማይገቡና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ምሰሶ መሆኗን ያረጋገጡበት ነበር ብሏል። በሱዳን በኩል ሸሽተው የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ሱዳን ትብብር እንደምታደርግ ማሳወቋም በመግለጫው ተነግራል። የግብፅና የሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድን በተመለከተም የሁለቱ ሀገራት ልምምድ በኢትዮጵያ ኪሳራ እንደማይሆን ኢትዮጵያ እንደምታምንና ሱዳንም ደቡብ ሱዳንም ይህንን እንደሚያራምዱ ለኢትዮጵያ ማረጋገጣቸው በመግለጫው ተገልጿል።