80 በመቶ የጣና ሐይቅ የእምቦጭ አረም ተነቅሏል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

የእንቦጭ አረም ለማስወገድ ለአንድ ወር በቆየው ዘመቻ ከ4 ሺህ 300 ሄክታር መሬት ውስጥ 80 በመቶው የሚሆነው አረም እንደተወገደ ተገልጿል።

የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጄንሲ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር አያሌው ወንዴ እስከ ሕዳር 20 ድረስ አረሙን የማስወገዱ ስራ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

አረሙ ላለፉት ዓመታት በሐይቁ ላይ ዘሩን ስለጣለ ክትትል እንደሚያስፈልገው በመጥቀስም አካባቢውን በነባር ዕፅዋት መተካትና ልቅ ግጦሽን መከላከል እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል፡፡

ለዘመቻው የገንዝብ ድጋፍ የሚያደርጉና ገንዘቡን ያልከፈሉ የክልልና የፌደራል ተቋማት ገንዘቡን እንዲከፍሉም ጠይቀዋል። እስካሁን 260 ሺህ ዜጎች በዘመቻው ሲሳተፉ በቀን ከ2 ሺህ እስከ 14 ሺህ ዘማቾች ተሳታፊ ሆነዋል። (አብመድ)