መረጃ ለመስጠት የማይተባበሩ ተቋማትና ግለሰቦች በሕግ ይጠየቃሉ – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


(ኢዜአ) የመንግሥት የመሬት ይዞታዎችን በመለየት ስራ መረጃ ለመስጠት የማይተባበሩ ተቋማትና ግለሰቦች በሕግ እንደሚጠየቁ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ።
የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የፌዴራል አስፈፃሚ ተቋማትን እንደገና ለማደራጀት በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሆኖ የተቋቋመ የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት ነው።
Image may contain: 2 people, closeup and text

ወይዘሮ መሰረት አባተ — አቶ ጫኔ ሽመካ

ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት የመሬት ይዞታዎችን የመለየት፣ የመመዝገብ፣ ልኬታቸውን የማወቅና የማልማት ሥልጣን ተሰጥቶታል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ መሰረት አባተ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት ይዞታ የሆነን መሬት በማደራጀት የሕዝብና የአገርን ፍላጎት መሰረት አድርጎ የሚያለማ ነው።
ለዓመታት ታጥረው ነገር ግን አገልግሎት የማይሰጡ የመንግሥት የመሬት ይዞታዎች በአገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይም ተጽዕኖ አሳድረዋል ብለዋል።
በመሆኑም የመንግሥት የመሬት ይዞታዎች የሚፈለገውን አይነት ልማት በአግባቡ ማስመዝገብ እንዲችሉ ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል ይላሉ የምክር ቤቱ አባላት።
የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጫኔ ሽመካ የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን የመሬት ይዞታዎችን ለመለየትና ለማደራጀት የሚሄድባቸው ተቋማት መተባበር አለባቸው ብለዋል።
መረጃ የሚጠየቁ የፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች የተቋሙን ዓላማ በአግባቡ ተረድተው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡም አሳስበዋል።
ከዚህ ባሻገር ኮርፖሬሽኑ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች ለመስጠት የማይተባበሩ ግለሰቦችና የመንግሥት ተቋማት አዋጁን እንዳልተቀበሉ ይቆጠራል ነው ያሉት።
የአገሪቱ ከፍተኛው የሕግ አውጪ አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀውን አዋጅ ገቢራዊ አለማድረግ ሕግ መጣስ በመሆኑ መረጃ ለመስጠት የማይተባበሩ ሁሉ ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል።