መተከል ዞን በማዘዣ ትዛዝ ሥር እንዲተዳደር ተወሰነ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


መተከል ዞን በማዘዣ ትዛዝ ሥር እንዲተዳደር ተወሰነ። በመተከል ዞን የደረሱ ጥቃቶችን አስመልክቶ ከአማራና ቤንሻንጉል ክልሎች መሪዎች ጋር መወያየታቸውን ጠ/ሚኒስት ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ውስጥ አልፎ አልፎ ከሚከሰቱ ችግርች በስተቀር አንፃራዊ መረጋጋት መስፈኑን ደግሞ የክልሉ ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ፤ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮነን በተገኙበት ውይይት ከተካሄደ በኋላ ዞኑ በማዘዣ ማዕከል ትዕዛዝ ሥር እንዲተዳደር ተወስኗል ብለዋል።

ማኅበረሰቡ አብሮነቱን አጠናክሮ የሚመጣበትን ማናቸውንም ጥቃት መመከት የሚያስችል ሥራ መሰራት እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰናል ሲሉም ተናግረዋል። በዞኑ ሰባት ወረዳዎች ስልጠና የወሰዱ ነባርና አዳዲስ ሚሊሻዎችም ከፀጥታ አካላት ጎን ሆነው ሰላም ለማስፈን ይሠራሉ ብለዋል ኃላፊው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።