የወር ደሞዛችንን በሁለት ዓመት ተከፍሎ በሚያልቅ ክፍያ ገበታ ለሀገር ስጡ ተብለናል: አልተስማማንም – የንግድ ባንክ ሰራተኞች ቅሬታ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ገበታ ለሀገር” ለተሰኘው ፕሮጀክት ከባንክ ሰራተኞች የሚጠየቀው መዋጮ አንዳንድ ቅሬታ እያስነሳ እንደሆነ የሚደርሱኝ መልእክቶች ይጠቁማሉ!
“የወር ደሞዛችንን በሁለት ዓመት ተከፍሎ በሚያልቅ ክፍያ ስጡ ተብለናል፣ ችግሩ በሚድያ ሲገለፅ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ነው መባሉ ነው። ይህ ስህተት ነው፣ በማናጀሮች ካላዋጣችሁ እድገት ቢመጣ ላታገኙ ትችላላችሁ ወዘተ እየተባልን ነው” የሚል መረጃ ያደረሰኝ የባንክ ሰራተኛ አለ።
“በቀጥታ አይደለም እንጂ ተፅእኖ አለ፣ በተለይ ከማኔጅመንት ውጭ ያሉት ደሞዛቸውም ስለሚያንስ ቅሬታ አላቸው። በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ለማለት ያስቸግራል” ያለኝ ሌላኛው ሰራተኛ ነው።
“ፕሮጀክቱ ሀገራዊ ስለሆነ ብዙ ሰራተኛ በፈቃደኝነት ሊሳተፍ ይችላል፣ እየሆነ ያለው ግን በተቃራኒው ነው። ‘አዋጣለሁ’ ወይም ‘አላዋጣም’ የሚል ፎርም ሙሉ ተብለህ ‘አላዋጣም’ ብትል የሚከተለውን መገመት ይቻላል። በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ቢሆን ኖሮ ፈቃደኛ የሆናችሁ ብቻ ፎርም ሙሉ ይባል ነበር” ብሎ መልእክት ያደረሰኝ አለ።
ቅሬታው የንግድ ባንክ ሰራተኞች አካባቢ የበዛ ነው፣ በጉዳዩ ዙርያ ባንኩን ለማናገር ያረግኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም።
Source Elias Meseret