ባሕር ዳር አዲስ ከንቲባ ተሾመላት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ባሕር ዳር ከተማ አዲስ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በዛሬው ዕለት ተሹሞላታል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በቀድሞው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ መሐሪ ታደሰ (ዶ/ር) ምትክ ድረስ ሳኅሉን (ዶ/ር) ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

በአስቸኳይ ጉባኤው የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፍትሐነገሥት በዛብህ፣ የተጀመሩ ሥራዎች በአግባቡ እንዲፈፀሙ፣ የቤት መሥሪያ ቦታ ያላገኙ የቤት ማኅበራት እልባት እንዲሰጣቸው፣ በከተማ መስፋፋት የተነሡ አርሶ አደሮች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ፣ የባሕር ዳር የዘላቂ የውኃ አገልግሎት እንዲሻሻል እና የሥራ ዕድል ፈጠራና የሥራ እድል ፈላጊ አለመመጣጠን በትኩረት እንዲሠራበት ማሳሰባቸውን አማራ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።