የዝቋላ አቦ መንፈሳዊ ተጓዦች ደብረዘይት ላይ እየተንገላቱ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ፣ ከአሰላ እና ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ዝቋላ በመሄድ ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ከቢሾፍቱ ወደ ዝቋላ በሚወስደው መንገድ ላይ አትሄዱም ተብለው ተከልክለዋል የሚል መረጃ ትናንት በስፋት ወጥቷል።
ኢትዮጵያ ቼክ ትናንት ወደ ዝቋላ አቦ ያመሩ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ቦታው ለመድረስ 20 ኪሎሜትር አካባቢ ሲቀራቸው እንዲቆሙ መደረጉን ከጎዶሊያስ የጉዞ ማህበር እና ከሌሎች ሁለት ተጓዦች አረጋግጧል።
ከአዲስ አበባ መንፈሳዊ ተጓዦችን ይዞ ወደ ዝቋላ ያመራ የነበረው የጎዶሊያስ የጉዞ ማህበር እንደገለጸው አውቶብሶቹ እንዲቆሙ በመደረጉ መንገደኞች ለሰዐታት በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል፣ አውቶብሶች ለምን እንዲቆሙ እንደተደረ ምክንያት እንዳልተነገራቸውም ጨምረው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ቼክ ያናገራቸው ሌሎች ሁለት ተጓዦች ደግሞ አውቶብሶች እንዲቆሙ መደረጋቸውን አረጋግጠው ወደ ዝቋላ አቦ በእግራቸው ለመጓዝ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
ከትናንት በስቲያ ግን መንፈሳዊ ተጓዦችን ይዘው ወደ ዝቋላ ያመሩ ተሽከርካሪው ወደ መዳረሻቸው ካለምንም ችግር መድረሳቸውን ሰምተናል።
ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ቼክ ጥያቄ የቀረበለት የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ፣ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ወደ ዝቋላ አቦ የሚሄደውን ሰው ቁጥር ለመቀነስ ትናንት ከሰዐት በኅላ ጀምሮ ተሽከርካሪዎች እንዲቆሙ መደረጉን ገልጿል። ክልከላው ዛሬም በከፊል መቀጠሉን መምሪያው ጨምሮ አስታውቋል።
የኔ ጥያቄ: ምክንያቱ ይህ ነው ከተባለ ይህን ሁሉ ህዝብ እንዲህ ከማጉላላት ቀድሞ ማሳወቅ አይሻልም? የመስቀል እና ኢሬቻ በአላት ሊከበሩ ሲል የአዲስ አበባ መግቢያ መንገዶች ሲዘጉም ተመሳሳይ ችግር ነበር፣ ቀድሞ ማሳወቅ የብዙዎችን እንግልት ማስቀረት ይችል ነበር።
☆ ይህ መረጃ የቀረበላችሁ የኢንተርኒውስ ፕሮጀክት በሆነው ኢትዮጵያ ቼክ ነው።