ለኢትዮጵያ የፖለቲካዊ ቀውስ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር ውይይት በአስቸኳይ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።

ለኢትዮጵያ የፖለቲካዊ ቀውስ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር ውይይት በአስቸኳይ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው በርሊን የሚገኘው የጀርመን እና የአፍሪቃ ትብብር በጀርመንኛው «ዶች አፍሪቃ ሽቲፍቱንግ ፈራይን» የተባለው ድርጅት ኢትዮጵያውያንና የጀርመን ምሁራንን እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት ዲፕሎማቶችንና ሌሎች ባለሙያዎችን በጋበዘበት የኢንተርኔት የውይይት መድረክ ላይ ነው።

«መስቀለኛ መንገድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የፖለቲካ የሽግግር ሂደት እና ከአሳሳቢው የፖለቲካ ቀውስ መውጣት የሚቻልባቸው አማራጭ መፍትሄዎች» ላይ በመከረው በዚህ ውይይት ላይ ከቀረቡትአማራጮ መፍትሄዎች መካከል፤ ሀገሪቱ ለገባችበት ፖለቲካዊ ቀውስ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር ውይይት በአስቸኳይ ማካሄድ፤ በፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልልና በአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የተፈጠሩ ውዝግቦችን በውይይት መፍታት፤ ነፃና ገለልተኛ የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት፤ ተአማኒነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ሀገራዊ ምርጫን ማካሄድ ይገኙበታል።

ሥርዓት አልበኝነትን ለመከላከል ለወጣቱ አማራጭ የሥራ ዕድሎችን ማስፋፋት፤ የዜጎችን የመኖር ዋስትናን ማረጋገጥና ሕገ-መንግሥቱን ማሻሻል አልያም አተገባበሩ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚሉት አማራጮችም መጠቆማቸውን ውይይቱን የተከታተለው የDW ዜና ያስረዳል።