የአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት ከበባ አበቃ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW : ለሁለት ቀናት በጸጥታ ኃይላት ከተከበበው ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር መሪ ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት ለመውጣት የሞከሩ 15 የሚሆኑ የሃገር ሽማግሌዎችና ዛሬ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ኦነግ አስታወቀ።

በሌላ በኩል ትናንትና ከትናንት በስቲያ ከስፍራው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው የተወሰዱ 10 ሰዎች ትናንት ማምሻውን መለቀቃቸውን በአቶ ዳውድ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነኝ ያሉት አቶ በቴ ዑርጌሳ ለዶይቼ ቬለ ገለጸዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት ነበሩ የተባሉ እንግዶች በሙሉ ከወጡ በኋላ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ስፍራውን ለቀው መሄዳቸውም ተገልጿል።አቶ ዳውድ ኢብሳም በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚገኙ አቶ በቴ ዑርጌሳ ተናግረዋል።

ዶቼቬለ ስለ ጉዳዩ የጠየቃቸው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጀኢላን አብዲ ጉዳዩን ገና አለማጣራታቸውን እንደተናገሩ DW ዘግቧል።