ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተገናኘ በ114 መዝገቦች ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተገናኘ በተለያዩ ቦታዎች በተፈጠረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በ2 ወር ውስጥ በቅንጅት የምርመራ ስራ በማከናወን በፌዴራል ደረጃ በ114 መዝገቦች ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በእቅድ ዝግጅት ምዕራፍ፣ ሕግን ከማስከበር እና የወንጀል ህጉን ከማስፈጸም እንዲሁም የሕግ ማዕቀፎችን አስመለክቶ በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻፀምን አስመልክተው መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት በዝግጅት ምዕራፍ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ማዘጋጀትና በዕቅዱ ላይ ከተቋሙ ሰራተኞች እና ከባለድረሻ አካላት ጋር በየርዕሰ ጉዳዩቹ ምክክር እና ውይይት የተደረገ መሆኑን ገልጸው ተቋሙ አዲስ አደረጃጀት በመዘርጋት ትኩረት የሚሹ የሥራ ዘርፎችን የሚከውኑ የሥራ ክፍሎችን አቋቁሟል፡፡ በዚህም መሠረት በሴቶችንና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚከታተል ዳይሬክቶሬት መቋቋሙን ጠቅሰው የክልሎችን ቅንጅታዊ አሰራር የሚከታተል እና ድጋፍ የሚሰጥ አዲስ የሥራ ክፍል እንዲሁም የንቃተ ህግ ትምህርን በልዩ ትኩረት የሚሰጥ ዳይሬክቶሬት መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አክለውም ተቋሙ በሕግ ከተሰጠው ተልዕኮ መካከል ዋንኛው ሕግን ማስከበርና እና የወንጅል ሕጉን ማስፈጸም ሲሆን የወንጀል ጉዳዮችን ማጣራት፣ ምርመራ ማድረግ እና ክስ መመስረት በመሆኑ በዚሁ ስልጣኑ መሰረትም በመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት 12,239 መዝገቦች ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለውሳኔ የቀረቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በ12,037 መዝገቦች ላይ ውሳኔ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
ወደ ዐቃቤ ሕግ ከተመሩ መዝገቦች መካከል በፍርድ ቤት ክርክር እየተደረገባቸው ያሉ 33,714 መዝገቦች ላይ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ክርክር የተደረገ ሲሆን በ3 ወራት ውስጥ የመጨረሻ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኙ 2480 መዝገቦች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ በ2371 መዛግብት ላይ ተከሳሾቹ የጥፋተኛነት ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆኑን ተናግረው ቀሪዎች ተከሳሾች በነጻ እንደተሰናበቱ ጠቁመዋል፡፡
በተቋሙ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከተሰሩ ተግባረት መካከል የኢኮኖሚ ወንጀሎች በተመለከተ ጥፋተኛ ተብለው የተያዙ ሰዎችን በፍርድ ውሳኔ መሰረት ማስቀጣት ብቻ ሳይሆን በወንጀል ስራቸው ያገኙትን ሀብት ይዘው እንዳይቀጥሉ በማድረግ ሀብት የማስመለስ ተግባር ላይ አትኩሮ የሚሰራ የስራ ክፍል በአዲስ መልክ የተደራጀ መሆኑን እና የስራ ክፍሉ በሰራው ስራ 412 ሚሊዩን ብር የሚገመት ገንዘብ ወደ መንግስት ለማስመልስ በሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተገናኘ በተለያዩ ቦታዎች በተፈጠረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በ2 ወር ውስጥ በቅንጅት የምርመራ ስራ በማከናወን በፌዴራል ደረጃ በ114 መዝገቦች ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በሕግ ማዕቀፍ ሕጎችን ከማዘመን ጋር በተያያዘ የተሰሩ የሕግ ጥናቶችና ማሻሻያዎችን አስመለክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡