የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑ ተገለጸ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
በኢትዮጵያ በቅርቡ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ መምጣቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ በሰጡት መግለጫ ከሶማሌላንድ፣ ከየመን እና ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የገባው የአንበጣ መንጋ የተለያዩ አካባቢዎችን መውረሩንም ተናግረዋል፡፡
የአንበጣ መንጋውን የመከላከል ስራ እየተከናወነ ቢሆንም የመርጫ አውሮፕላኖች እጥረት ባለመቀረፉ ችግሩ ይባባሳል የሚል ስጋት መኖሩን ጠቁመዋል፡፡
ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ለማግኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላትም የአንበጣ መንጋውን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ርብርብ እንዲያደርጉ ዶ/ር ማንደፍሮ ጠይቀዋል፡፡

በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ያጋጠመውን የበርሃ አንበጣን መንጋ ለመከላከል እስከ 10 አውሮፕላኖች እና 150 የመስክ ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልጉት ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ መንጋውን ለመከላከል የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስቧል፡፡

መንጋው በአሁኑ ወቅት በአፋር፣ በሱማሌ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች ተከስቷል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በሚኒስትሩ የሚመራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ተባዩን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርርብ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዎች ክልሎችን ተከፋፍለው ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሰው ሃይል እና በተሽከርካሪ በሚንቀሳቀስ መርጫ መሳሪያ እና አውሮፕላን በመታገዝ የጸረ ተባይ ኬሚካል ርጭት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተሽከርካሪን ጨምሮ መንጋውን የመቆጣጠር ጥረቱን ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ በሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል ዶ/ር ማንደፍሮ፡፡

በቅርቡ ተጨማሪ ስምንት አውሮፕላኖች ከውጭ ገብተዋል፡፡ በመካሄድ ላይ ያለውን ርጭት ለማገዝ የሚያስችል ዝግጅት በማድረግም ላይ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር ማንደፍሮ አሁን ባለው ትንበያ መሰረት የተባዩ ክስተት ለተወሰኑ ጊዜያት ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል ብለዋል፡፡

እሱን ለመከላከል 10 አውሮፕላኖች እና 150 የመስክ ተሽከርካሪዎች ያስፈልጋሉ ያሉም ሲሆን አስፈላጊውን ሁሉ ለማሟላት ከተለያዩ ተቋማትና ሀገራት ጋር መንግስት እየተነጋገረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከአርሶና አርብቶ አደሩ ጀምሮ ሁሉም አካላት መንጋው ወደ ሰብል አምራች አካባቢዎች ተስፋፍቶ የመኸር ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ርብርብ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አል ዐይን አማርኛ ከሰሞኑ በባለፈው የምርት ዘመን ይጠበቅ ከነበረው ምርት ውስጥ 1 በመቶው ወይም 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ገደማ ምርት በአንበጣ መንጋ ወድሟል ሲል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡