በኢትዮጵያ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኢትዮጵያ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ
DW : የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ትናንት እንደገለፀው በኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሽታ ፣የበረሃ አንበጣ ባደረሰው ጉዳት እንዲሁም በጎርፍ አደጋ ሳቢያ 15.1 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ይፈልጋሉ።
No photo description available.ይህ ቁጥር እያደገ ሊሄድ እንደሚችል ድርጅቱ ጠቁሞ፤ለእነዚህ ዜጎች ምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ ዘገባው አመልክቷል።
በሀገሪቱ የኮሮና ወረርሽኝ እስከ ሀምሌ መጀመሪያ 330 ሺ የስራ ዕድሎችን ያሰናከለ ሲሆን የሀገሪቱ መንግስት ሥራ አጥነትን ለመቀነስ በጎርጎሪያኑ ከ2020 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጉ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ተስፋ ቢያደርግም የበሽታው መስፋፋት ይህንን ዕቅድ ያደናቅፈዋል ሲል ድርጅቱ አመልክቷል።
በሌላ በኩል በሀገሪቱ የአንበጣ መንጋ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት ማውደሙንም የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ገልጿል።