የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና የተፈሪ መኮንን ቀድሞ ተማሪዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 206 ነዋሪዎች ድጋፍ አደረጉ  


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኮሌጁ ማህበረሰብ ድጋፉን ያደረገው በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የኮሌጁ ተማሪዎች 253ሺ600 ብር እና የኮሌጁ ማህበረሰብ 35ሺ ብር በድምሩ ከ288ሺ 600 ብር በመሰብሰብ ለ206 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፋቸውን አድርገዋል፡፡

በድጋፉ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አማካሪ ወ/ሮ ባንቺ ተሾመ የኮሌጁ ማህበረሰብና የቀድሞ ተፈሪ መኮነን ለወገናቸው ያደረጉት ድጋፍ ለሃገርና ህዝባቸው በችግር ጊዜ ደርሰው ድጋፍ በማድረጋቸው በአስተዳደሩ ስም ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የእንጦጦ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን ወ/ሮ ዋጋየ ገ/መድህን ኮሌጁ ከቀድሞ የተፈሪ መኮነን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማህበር ጋር በመቀናጀት መንግስት ባደረገው የማእድ ማጋራት ጥሪን ተቀብሎ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሃገራችን ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ለ3ኛ ጊዜ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በተደረገው ድጋፍ ለ206 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ግራም ዱቄት፣5ኪሎ መኮረኒ፣5 እሽግ ፓስታ፣ 3ሊትር ዘይት እና 2 የአፍ መሸፈኛ ማስክ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ምንጭ፦ ጉለሌ ፕሬስ