መስከረም ሁለት የአብዮት በዓል በነበር ከቀሩ ባለታሪክ ቀኖች አንዱ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢትዮጵያ ትቅደም ! ….. ያለምንም ደም ! …… አቆርቋዥ ይውደም ! …
መስከረም ሁለት የአብዮት በዓል በነበር ከቀሩ ባለታሪክ ቀኖች አንዱ
መስከረም 2 ሰው ጎዳና የሚሞላበት የፌሽታ ቀን ነበር፡፡ ዛሬ አብዮት አደባባይ ቦታው እንጂ ስሙ የለም፡፡ ዛሬ ይሄ ግዙፍ የሀገሪቱ ጎዳና ደመራ ሲበራ ብቻ የሚደምቅ ስፍራ ሆኗል፡፡ ዛሬ መስከረም ሁለተኛው ቀን የበዓል ማግስት ብቻ ሆኖ በሌላ ትውልድ በአንጎቨር ሳቢያ እስከ ረፋድ የሚተኛበት ቀን ሆኖ አርፏል፡፡ ትናንትና በዚህ ቀን ማንም አይተኛም፤ መስከረም ሁለት በዘመኑ ማልዶ የሚቀሰቅስ የክት ቀን ነበር፡፡ ቀን ቀንን ጣለው፤ መስከረም ሁለት ከደመቀው ክቡሩ ወርዶ የዘመን መለወጫው ማግስት ሆነ፡፡ዛሬ ተራ ቀን ሆነ፡፡
ዛሬ ግን መስከረም ሁለት ቀን ነበር፡፡ በነበር ከቀሩ ባለታሪክ ቀኖች አንዱ መጨረሻው ይኽው የአዲስ ዓመት ማግስት ሆኖ ቀረ፡፡ በዘመኑ መስከረም ሁለት ማግስት አልነበረም፡፡ ይልቁንም መስከረም አንድ ዋዜማ ነበር፡፡
.
ሀገር ዳሷን ጥላ ሽር ጉድ የምትልበት ቀን መስከረም ሁለት እንዳልነበር ዛሬ ይህ ቀን የአዲሱ ዓመት ድባብ ሲነጋ የሚያንዣብብበት ሆነና አረፈው፡፡ መስከረም ሁለት ባለ አደባባይ ነው፡፡
.
መስከረም ሁለት ሰው ጎዳና የሚሞላበት የፌሽታ ቀን ነው፡፡ መስከረም ሁለት ሰማያዊ ለባሽ ኮሚኒስቶች ከፍ ካለው ስፋራ ቆመው ግራ እጃቸውን ወደ ሰማይ የወረወሩበት የደስታ ቀን ነው፡፡ ዛሬ አዘቦት ሆኗል፡፡ ተራውን ለነ ግንቦት ሃያ የሰጠ መጻተኛ ቀን፤ በዚህ ሰዓት በዚያ ዘመን ራዲዮ ስለ ድል ያወራል፡፡ ጥላሁን ገሰሰ ይለያል ዘንድሮ ይላል፡፡ ከያኒያን አብዮቱን በአብዮት አደባባይ ያደምቃሉ፡፡
.
የመጨረሻው ንጉስ መጨረሻ የሌለው ሐጢአት ይተነተናል፡፡ ቀኑ መስከረም ሁለት ነው፡፡ ሰዎች ማልደው ከየቤታቸው ወጥተው አብዮት አደባባይ ቆመዋል፡፡ አ.ኢ.ሴ.ማ.ዎች፣ መ.ኢ.ገ.ማ.ዎች፣ አ.ኢ.ወ.ማ.ዎች፣ ኢ.ሰ.ፓ.ዎች በዚህ ዘመን ብዙዎች አብዮት ተባሉ፡፡ መስከረም ከሰላሳው ቀን መገለጫነት ተገድቦ የመስከረም ሁለት መለያ የወል ስም ሆነ፡፡
.
ዛሬ አብዮት አደባባይ ቦታው እንጂ ስሙ የለም፡፡ ዛሬ ይሄ ግዙፍ የሀገሪቱ ጎዳና ደመራ ሲበራ ብቻ የሚደምቅ ስፍራ ሆኗል፡፡ ዛሬ መስከረም ሁለተኛው ቀን የበዓል ማግስት ብቻ ሆኖ በሌላ ትውልድ በአንጎቨር ሳቢያ እስከ ረፋድ የሚተኛበት ቀን ሆኖ አርፏል፡፡ ትናንትና በዚህ ቀን ማንም አይተኛም፤ መስከረም ሁለት በዘመኑ ማልዶ የሚቀሰቅስ የክት ቀን ነበር፡፡ ቀን ቀንን ጣለው፤ መስከረም ሁለት ከደመቀው ክቡሩ ወርዶ የዘመን መለወጫው ማግስት ሆነ፡፡ ( #ሔኖክ_ስዮም_በድሬትዩብ) #MinilikSalsawi