ዓመቱ በመልካምነቱ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን በእኩል የሚያስተናግዱ መሪዎችን ማየት የቻልንበት ነው – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
ዓመቱ በመልካምነቱ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን በእኩል የሚያስተናግዱ መሪዎችን ማየት የቻልንበት፤ የሙስሊሙ ጥያቄዎች የተመለሱበት ነው.. ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር
Image may contain: 1 person, sitting and shoes(ኢዜአ) – 1ሺህ 441ኛው የኢድ አል- አድሃ በዓል ፈጣሪን በሚያወድሱ ዜማዎች(ተኪብራ)ና በፀሎት( ሶላት) በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጂድ ዛሬ ተከብሯል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምከር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር በዓሉን በማስመልከት መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ዓመቱ በመልካምነቱ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን በእኩል የሚያስተናግዱ መሪዎች ማየት የቻልንበት፤ የሙስሊሙ ጥያቄዎች የተመለሱበት መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን በአንድነት እየገነቡት ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት የጀመረበት ዓመት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከስቶ የእምነት ቦታዎችን ያዘጋው የኮቪድ ወረርሽኝ አሳሳቢና አስጨናቂ የሆነበት ዓመት ነው ሲሉም ብለዋል።
ወረርሽኙን ለመከላከል ጥንቃቄውን እንዳያጓድል በተለይም ሙስሊሙ ለፈጣሪ ዱኣ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።
ከእርስ በእርስ መነቋቆር በመውጣት የአገርን አንድነት መጠበቅ፤ ስላምና ልማትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሐጂ ሱልጣን አማን የኢድ በዓል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ባስጨነቀበት ወቅት ቢሆንም፤ አቅመ ደካሞችን የመርዳት ባህላችን ለአፍታም መዘንጋት የለበትም ብለዋል።
የሙስሊሙ ማህበረሰብ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚያደርገው ድጋፍ እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል።
የእምነቱ ተከታዮች የተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳፏአቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።ዘንድሮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመከሰቱ በሳዑዲ ዓረቢያ በየዓመቱ የሚካሄደው የሐጅና ዑምራ ተጓዦች ወደ ሥፍራው አልተጓዙም።ሳዑዲ ዓረቢያ ከውጭ ለሚገቡ ተጓዦችም ቪዛ አልሰጠችም።