ትራምፕ የ2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲራዘም ጠየቁ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ዶናልድ ትራምፕ ህዳር ላይ የሚካሄደው የ2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲራዘም ጠየቁ።

Donald Trump suggests delay to 2020 US presidential election

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ምርጫው እንዲራዘም የጠየቁት፥ በፖስታ አማካኝነት የሚደረግ ምርጫ ለማጭበርበር አመቺ በመሆኑ እና ተአማኒ የሆነ ውጤት ለማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን ነው ብለዋል።የአሜሪካ ግዛቶች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፖስታ የታገዘ እንዲሆን ጠይቀው እንደነበረ አይዘነጋም።

Donald Trump has called for November’s presidential election to be postponed, saying increased postal voting could lead to fraud and inaccurate results.He suggested a delay until people can “properly, securely and safely” vote.There is little evidence to support Mr Trump’s claims but he has long railed against mail-in voting which he has said would be susceptible to fraud. US states want to make postal voting easier due to public health concerns over the coronavirus pandemic.

ስድስት የአሜሪካ ግዛቶች በፖስታ መልእክት የታገዘ ምርጫን ለማድረግ እቅድ ይዘው የነበረ ሲሆን፥ እቅድ የያዙ ግዛቶችም ኡታህ፣ ሀዋይ፣ ኮለራዶ፣ ኦሬገን እና ዋሽንግተን ናቸው። በዚህም ግዛቶቹ የፖስታ ድምጽ መስጫዎችን ለመራጮች የሚልኩ ሲሆን፥ መራጮቹ የሰጡት ድምጽም በምርጫው ቀን ተመልሶ የሚላክ ይሆናል ነው የተባለው።

ከዚህ ጎን ለጎን ግን በጣም በተወሰኑ ቦታዎች ላይ በአካል በመሄድ የሚደረግ የድምጽ መስጠት ሂደት ይኖራልም ነበር የተባለው።
ሆኖም ግን በፖስታ መልእክት የሚደረግ ምርጫ ግለሰቦች ከአንድ ጊዜ በላይ ድምጽ እንዲሰጡ ያደርጋል የሚል ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል።ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም በፖስታ የሚደረግ ምርጫ የመጭበርበር እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ባለፉት ቀናት ሲገልፁ እንደነበረም ነው የተነገረው።
ይህንን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ላይ በፖስታ የሚደረግ ምርጫ የ2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ተአማናኒት የሚያሳጣ እና የተጭበረበረ ሊያደርገው እንደሚችል ገልፀዋል።ስለዚህም የአሜሪካ ህዝቦች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ እና በአግጋቡ ምርጫን ማካሄድ እስኪችሉ ድረስ የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲራዘም ጠይቀዋል።
=
ምንጭ፦ BBC.COM