ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጠሩ ፓርቲዎች ስለ ፓርቲው እድሜ ብቻ የሚጨነቅ ህወሓት ብቻ ነው – ዶ/ር አብርሃም በላይ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
“ፓርቲን ለማስቀጠል ህዝብን እንደ ከለላ የሚጠቀም ከህወሓት ውጪ በየትኛውም ዓለም ማግኘት አይቻልም”
  ዶክተር አብርሃም በላይ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራርና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
Image may contain: 1 person, suit(ኢ ፕ ድ) – ፓርቲን ለማስቀጠል ህዝብን እንደ ከለላ የሚጠቀም ህወሓት ብቻ መሆኑን ፤ የትግራይ ህዝብ ታሪኩ፣ በህይወት መስዋእትነት ያረጋገጠው መብቶቹና ሰላሙ ለአፍታም እንዲዛቡበት እንደማይፈልግ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አስታወቁ ።
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራርና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጠሩ ፓርቲዎችም ስለ ፓርቲው እድሜ ብቻ የሚጨነቅ ህወሓት ብቻ ነው።የፓርቲ እድሜ ለህዝብ ለመስጠት የሚያደርጉት ጥረት በጣም አሳፋሪና ህዝብን የናቀ ነው፤ የትም ዓለም ብንሄድ ፓርቲን ለማስቀጠል ህዝብን እንደ ከለላ የሚጠቀም ከህወሓት ውጪ ማግኘት አይቻልም።
ህወሓት በዚህ ሰዓት የክልሉን ፣ የአገራችን፣ የአከባቢውን እንዲሁም ዓለማቀፍ ሁኔታዎችን የመተንተንና የመረዳት ከፍተኛ ጉድለት ያለበት ፓርቲ ሆኖ ነው የማየው ያሉት ሚኒስትሩ ፣ ሁኔታዎችን የሚመረምርበት፣ የሚቃኝበትና የሚረዳበት ነገር በትክክል ሳይንሳዊ በሆነ መልኩና እውነታውን ይዞ የሚንቀሳቀስ ሆኖ አይታይም ብለዋል ።
እንደ ዶክተር አብርሃም ማብራሪያ ፤ የፖለቲካ ልህቀት የሚወሰነው አንደኛ የሚወክለውን ማህበረሰብ በማወቅና መረዳት እንደመሆኑ ይህንን ማወቅና መረዳት በጣም ያስፈልጋል። ሁለተኛ ከጊዜው ጋር የተቃኘ የፍላጎት አረዳድና ግንዛቤ መያዝ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር የሚስማማ አዲስ ሀሳብና ፕሮግራም ማፍለቅን የሚጠይቅ ነው። እናም አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ንቃት አለው፤ ለህዝብ ይመጥናል የሚባለው በትንሹ እነዚህን ይዞ ሲገኝ ነው።