ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው
EBC : ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው።
ውይይቱ በመንግሥት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
በቀጣይም አገራዊ ምርጫን በሚመለከት ከዚህ በፊት ከተደረው ምክክር የቀጠለ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።
በዚህም እስከ ሰባት በሚደርሱ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ለማድረግ ስምምነት ተደርሷል፣ በቅድሚያ ግን ውይይት የሚደረግባቸው አራት አጀንዳዎችም ተለይተዋል።
በቅድሚያ አገራዊ መግባባት ላይ ውይይት ለማድረግ የተስማሙ ሲሆን፣ በዚህም ጉዳይ ላይ ገለጻ ለማድረግ እና ለማወያየት ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎች ተመርጠዋል።