ያልተቀደሰው ጋብቻ ፤ የድሐ ልጅ መሞት ለፅንፈኛ ዲያስፖራዎች ፖለቲካ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ያልተቀደሰው ጋብቻ ፤ የድሐ ልጅ መሞት ለፅንፈኛ ዲያስፖራዎች ፖለቲካ ነው።
ሕወሓትን ወደ ስልጣን ለመመለስ በውጪ የሚኖሩ የሕወሓት አባላት ደፋ ቀና እያሉ መሆናቸውን ሰሞኑን ከሽንፍላ ዘረኞች ጎን ተሰልፈው አይተናቸዋል። የኦሮሞ ደም በየሜዳው ሲፈስ የኦሮሞ ወጣቶች በየስርቻው ሲታረዱ በእሬቻው ቀን ወደ ገደል ሲወረወሩ የሕወሓት ሰውች አሸንዳዬ ሲጨፍሩ ነበር።
በሕወሓት የስልጣን ዘመን የኦሮሞ ሕዝብ ሲታሰር ሲገደል ሲሰደድ ሲንገላታ እናት በልጇ ሬሳ ላይ ተቀምጭ ስትባል ኢትዮጵያዊያን የዲያስፖራ ኮሚኒቲዎች የሕወሓትን አገዛዝ በመቃወም ሰልፍ ሲወጡ የሕወሓት አባላት የትግራይ ተወላጆች ግን ዝር ብለው አያውቁም። ሕወሓት በኦሮሞ ፖለቲከኞች ክፍተትና በደቡብ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች ላይ ሰርጎ ገብ በመሆን ሃገርን በማተራመስ ስልጣን ለመያዝ የምታደርገው ሩጫ ስለከሸባት በሰው አገር ሰልፍ መውጣት ጀምራለች።የደሃ ልጅ መሞት ለፅንፈኛ ዲያስፖራዎች ፖለቲካ ነው።
ሕወሐት በስልጣን ዘመኑ ያላረጋገጠውን መብት ዛሬ ላይ ለመብትና ለነፃነት ተከራካሪ ሆኖ መቅረቡና አደባባይ ላይ ሰልፍ መውጣቱ ከሕወሓት አይናውጣ ባሕሪ አንጻር ባያስደንቅም የኦሮሞ ሕዝብ ተከራካሪ የሆነበት ሞራል ግን አስገራሚ ነው። የሕወሓት ዲያስፖራዎች ባንድራቸውን ይዘው አደባባይ የሕዝብ መብት ተቆርቋሪ መሆናቸውን ማየት አስቂኝ ነገር ነው። ዳግም ወያኔን ወደ ስልጣን ለመመለስ የሚደረገው ሩጫ ባልተቀደሰው ጋብቻ ምክንያት የረከሰ መሆኑን የሕወሓት ሰዎች ሊያውቁ ይገባል። #MinilikSalsawi