ሕወሓት የራሱን ስልጣንና ጥቅም ለማስከበር ሲል ብቻ ሀገርን የሚበታትንበትም ሆነ የሚበጠብጥበት የህግ አግባብም ሆነ የሞራል ተቀባይነት የለውም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሀገር የመሆንና የትግራይ ሪፐብሊክን መመስረት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ከሆነ ሕጋዊ አግባብን ተከትሎ ያንን ማድረግ የሚቻል ቢሆንም እንደ ሕወሓት ያለ አምባገነን ቡድን ግን የራሱን ስልጣንና ጥቅም ለማስከበር ሲል ብቻ ሀገርን የሚበታትንበትም ሆነ የሚበጠብጥበት የህግ አግባብም ሆነ የሞራል ተቀባይነት የለውም ሲል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ::

የፓርቲው ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል በተለይ ለዶይቼ ቨለ “DW” እንደገለፁት ፤እንዲህ ዓይነቱ የሕዝቡ አጀንዳ ያልሆነ አፍራሽ እንቅስቃሴ የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሀገር ምስረታ ለረጅም ዘመናት የከፈለውን የመስዋዕትነት ታሪክ የሚያኮስስና አመራሩንም ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ነው ብለዋል::በሕዝብ ተቃውሞ የተወጠረው ሕወሓት በሰሞኑ የመቀሌ ስብሰባ የአንድ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭነቱን ለማስቀጠል “በትግራይ በቅርቡ አካሂደዋለሁ ከሚለው ክልላዊ ምርጫ በኋላ የራስን ሀገረ መንግሥት ወደ መመስረት ሂደት በመሸጋገር ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ልክ እንደ ሶማሊያ የጦር አበጋዞች በአቻነት ላይ የተመሰረተ ይሆናል” ሲል መደመጡ እየተጓዘበት ያለው የተሳሳተ መንገድ ተስፋ የመቁረጥ፣የአልሞት ባይ ተጋዳይነትና የጣዕረ ሞት እርግጫ መሆኑን አመላካች፤ ተራ ፕሮፓጋንዳና ቀረርቶ ነው ሲሉ ተችተዋል::

በአገሪቱ ምርጫ የማካሄድ ስልጣን የተሰጠው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ መሆኑ እየታወቀ ሕወሓት የክልል ምርጫ አካሂዳለሁ በሚለው አቋሙ መፅናቱን ኢ-ህገመንግስታዊ ነው ያሉት አቶ ነብዩ፤ መንግስትም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ሕገ-መንግሥቱ ሲጣስ በቸልታ እንደማይመለከቱት ገልፀዋል:: ይህ ዓይነቱ ድርጊት ከወንጀል ባሻገር ብዙ መዘዝ ሊያመጣ የሚችል በመሆኑ መንግሥት ተመጣጣኝ የሆነ የህግ እርምት በመውሰድ ሃላፊነቱን ይወጣል ሲሉም ነው ያስጠነቀቁት:: ለዝርዝሩ እንዳልካቸው ፈቃደ::የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል በተለይ ለዶይቼ ቨለ “DW” እንደገለፁት፤ ከለውጡ በኋላ ሕወሓት የተሰጠውን መልካም ዕድል ከመጠቀም ይልቅ አንባገነንነቱን፣ አፈናውንና ኃላፊነት የጎደለ ተግባሩን ገፍቶበታል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም በትግራይ በተለያዩ አካባቢዎች ከመልካም አስተዳደር እጦት፣ ከመሰረተ-ልማት አለመስፋፋት፣ ከስራ አጥነት እና ከአዲሱ የወረዳ አወቃቀር ጋር በተያያዘ የሚነሱ በርካታ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለማዳፈን በክልሉ በጣም አሳሳቢ እና ከፍተኛ የሆነ አፈና፣ ጭቆና፣ ብዝበዛና ግድያን መንሰራፋቱንም ነው ሃላፊው ጨምረው ያብራሩት። በሕዝባዊ ትግል የተገኘውን አገራዊ ለውጥ ተከትሎ የትግራይ ህዝብ ባለፉት ሁለት ዓመታት በትዕግሥትና በእርጋታ አገርን እያዳነ መቆየቱንም አቶ ነብዩ ገልፀዋል።.”ሕዝባዊ የለውጥ አመራሩን በመቃወም የትግራይን ሕዝብ ከኢትዮጵያ ለመነጠል በሕወሓት እየተደረገ ያለው እኩይ እንቅስቃሴ የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ምሥረታ ለበርካታ ዘመናት ያበረከተውን ጉልህ አስተዋፅዖ የሚያኮስስ ተግባር ነው” ሲሉም አስረድተዋል።.

በክልሉ ቅቡልነት የማይኖረው ምርጫ ለማካሄድ የሚደረገውን እንቅስቃሴም ኢ- ሕገ መንግስታዊና ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም ነው ያሉት::”በአገሪቱ ምርጫ የማካሄድ ስልጣን የተሰጠው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ መሆኑ እየታወቀ ሕወሓት የክልል ምርጫ አካሂዳለሁ በሚለው አቋሙ መፅናቱን ኢ-ህገመንግስታዊ ፤ መንግስትም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ሕገ-መንግሥቱ ሲጣስ ደግሞ በቸልታ አይመለከቱትም:: ይህ ዓይነቱ ድርጊት ከወንጀል ባሻገር ብዙ መዘዝ ሊያመጣ የሚችል በመሆኑ መንግሥት ተመጣጣኝ የሆነ የህግ እርምት በመውሰድ ሃላፊነቱን ይወጣል” ::

የትግራይ ሕዝብ የራሱን ሀገረ መንግሥት መመስረት ፍላጎቱ ከሆነ በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ሂደቱን ማከናወን የሚቻልበት አግባብ መኖሩ እየታወቀ በአፉ ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ምስረታ እታገላለሁ የሚለው ሕወሓት በሰሞኑ የመቀሌው ስብሰባ አምባገነን ገዢነቱንና ፈላጭቆራጭነቱን ለማስቀጠል “በትግራይ በቅርቡ ከሚካሄደው ክልላዊ ምርጫ በኋላ የራስን ሀገረ መንግሥት ወደ መመስረት ሂደት በመሸጋገር ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ልክ እንደ ሶማሊያ የጦር አበጋዞች በአቻነት ላይ የተመሰረተ ይሆናል” ሲል መደመጡ እየተጓዘበት ያለው የተሳሳተ መንገድ ተስፋ የመቁረጥና የአልሞት ባይ ተጋዳይነት የጣዕረ ሞት እርግጫ መሆኑን አመላካች እንዲሁምለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የታለመ በመሆኑ በተግባር የሚሞከር አይደለም::

ከሕዝብ ፍላጎት ውጪ ወደ ድርጊት ለመግፋት ከተሞከረ ግን ህጋዊ ተጠያቂነትንና ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሊያጤኑት ይገባል ሲሉ ነው አቶ ነብዩ ያስጠነቀቁት::”ሀገር የመሆንና የትግራይ ሪፐብሊክን መመስረት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ከሆነ ሕጋዊ አግባብን ተከትሎ ያንን ማድረግ የሚቻል ቢሆንም እንደ ሕወሓት ያለ አምባገነን ቡድን የራሱን ስልጣንና ጥቅም ለማስከበር ሲል ብቻ ሀገርን የሚበታትንበትም ሆነ የሚበጠብጥበት የህግ አግባብም ሆነ የሞራል ተቀባይነት የለውም”የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ለሕወሓት ተጨማሪ ዕድል እየሰጠው መሆኑን የጠቀሱት አቶ ነብዩ ፤ ሕዝቡ ይህን ማድረጉ ምናልባት ከውድቀታቸው ተምረው በተሻለ ሃሳብና አካሄድ በመጓዝ የአገርን ህልውና እና የትግራይን ህዝብ ተጠቃሚነትም ያስጠብቃሉ ከሚል ተስፋ እንደነበርም ተናግረዋል። ሆኖም ያ የመጨረሻ አንድ እድል እንዳበቃለት አሁን ላይ ግልጽ እየሆነ በመሄዱ በክልሉ በተለያየ መልኩ የህዝብ እንቢተኝነት እና የወጣቶች አመጽ በየአካባቢው እያየለ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤቱን በትግራይ ውስጥ አልከፈተም እንቅስቃሴም እያደረገ አይደለም የሚለውን የሕወሓት አመራሮች ትችትም ሃላፊው ውድቅ አድርገውታል::”በአፉ ለመድብለ ፓርቲ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እታገላለሁ የሚለው ሕወሓት፤በድፍረት የትግራይ ብልፅግና በክልሉ ውስጥ አይንቀሳቀስም ማለቱ “አፋኝነቱንና የፖለቲካ ምህዳሩን ማጥበቡን በአደባባይ በግላጭ ያስመሰከረበት ድርጊት በመሆኑ ሊያፍር በተገባው ነበር:: ለሁሉምፓርቲያችን የሚደርስበትን ማናቸውንም ጫና ሁሉ ተቋቁሞ በትግራይ መቀለ ቢሮ ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለሕብረተሰባችን ጤና ቀዳሚ ትኩረት በመስጠት የኮረና ወረርሽኝን በመከላከሉ ዙሪያ እንቅስቃሴያችን ለጊዜው በሱ ላይ ያተኮረ ቢሆንም ከዚሁ ጎን ለጎንም በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ አድማሳችንን ለማስፋትና ዓላማችንን ለማስተዋወቅ ተግተን እየሰራን ነው::” ሲሉ ለዶይቼ ቨለ አብራርተዋል::

የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ለትግራይ ሕዝብ በተለይ ለወጣቱ የሥራ ዕድልን ለማመቻቸት መሰረታዊ የልማት ችግሮቹን ለመፍታትና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ጥሩ ዕድል ይዞ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን የፓርቲው አደረጃጀት ከመቀለ እና አዲስ አበባ በተጨማሪ በቀጣይም በሌሎች ክልሎች በዞኖች እና በወረዳዎች በስፋት እንደሚዋቀር ይፋ ተደርጓል፡፡ በዲያስፖራም ጠንካራ ድጋፍ ሰጪ አባሎች እንዳሉት የጽ/ቤቱ ዋና ሃላፊ አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል ጨምረው አስረድተዋል:: DW