ግብፅ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃወሙ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 

Image may contain: indoor

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃውመውታል።

የአረብ ሊግ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ በዛሬው እለት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የአረብ ሊግ በስብሰባው ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብን ጨምሮ የሊቢያ ጉዳይንም በመመልከት ላይ ይገኛል።

በዚህ ስብሰባ ላይም የሊጉ አባል ሀገራት የሆኑት ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር የግብፅን ከታላቁ የውሳኔ ሀሳብን እንደማይቀበሉት አስታውቅዋል።