ልዮ መለያ ቁጥር ያላቸው የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ወደመጋዘን ገቡ – ምርጫ ቦርድ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሃሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሊያከናውነው አቅዶ ለነበረው አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ ለድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ግዥን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ቀድመው ወደመጋዘን ከገቡት የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶች በተጨማሪ የድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ወደመጋዘን እየገቡ ይገኛል፡፡ ለድምጽ መስጫ ቀን የተገዙ ቁሳቁሶች

1. ከግልጽ የሆነ ድምጽ መስጫ ሳጥን – 213,622
2. የሚስጥር ድምጽ መስጫ መከለያ – 156,600
3. የድምጽ መስጫ ቀን የአስፈጻሚዎች ቁሳቁስ- 58,400
4. ልዩ የምርጫ ቁሳቁሶች ማሸጊያ ፕላስቲክ ( plastic seal)  እና የእሸጋ ስራ ስቲከሮች – 798,300

ሲሆኑ ከነዚህም መካከል በመጀመሪያ ዙር የራሳቸው ልዮ መለያ ቁጥር ያላቸው የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ወደመጋዘን ገብተዋል፡፡ በቀጣይ ዙርም ቀሪዎቹ የድምጽ መስጫ ቀን ቁሳቁሶች መጋዘን ገብተው የሚጠናቀቁ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ