DW : የሃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች መቐለ በዝግ እየመከሩ ነው
–
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የሀገር ሽማግሌዎች በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ትግራይ ክልል መንግስት መካከል ያለው መልካም ያልኾነ ግንኙነት በንግግር እንዲፈታ ጥረት ለማድረግ ዛሬ መቐለ ገብተው በዝግ እየመከሩ ነው፡፡
–
የኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተው ይኽ ቡድን ዛሬ ጠዋት መቐለ ደርሶ በአኹኑ ወቅት ከትግራይ ክልል መንግስትና ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዝግ እየመከረ ነው።
–
ከሽማግሌዎቹና የትግራይ ክልል መንግስት አመራሮች ውይይት በኋላ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።