በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ለተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ መዛመት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምላሽ

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣቢያ በአንድ ግለሰብ ምክንያት ሳይገባ እንዳልቀረ በተጠረጠረ በህግ ጥላ ስር የነበሩ 40 ተጠርጣሪ እስረኞችን ጨምሮ 66 ሰዎች በኮሮና ተሕዋሲ መያዛቸው ተሰምቷል። መንግሥት የኮሮና ወረርሽን ያሳደረውን ስጋት ተከትሎ ቀደም ሲል በርካታ የህግ ታራሚዎችን እስከመልቀቅ እርምጃ ወስዶ ነበር ።…