አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ የዜጎችን መኖሪያ ቤት አፈረሰ

(ኢትዮጲስ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ስልጤ ሰፈር ቀጠና 8 አካባቢ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን መንግስት በኃይል አፍርሷል፡፡ ዜጎች ማረፊያ ማጣታቸውንም ገልፀዋል፡፡ የኮሮና ተህዋሴ በተስፋፋበትና ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ፆም ላይ ባሉበት ወቅት መጠለያ አልባ መሆናቸው ለተደራራቢ ችግር እንደዳረጋቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የፖርቲውን ፕሬዘዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች በቦታው ተገኝተው ተፈናቃዮችን አፅናንተዋል፡፡ የዜጎችን እንግልት ለመላው ኢትዮጵያዊያንና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ፓርቲያቸው እንደሚያሳውቅም ፕሬዘዳንቱ እስክንድር ነጋ በቦታው ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡ ንግግራቸውን ፖሊስ ለማስቆም ሲሞክርም ተስተውሏል፡፡ በህብረተሰቡ ጩኸት ግን ሊከሽፍ ችሏል፡፡

ከኮሮና ተህዋሴ እየተስፋፋ ባለበትና ዜጎች ቤት ውስጥ እንዲቀመጡ ባለሙያዎች እየመከሩ ባሉበት በዚህ ወቅት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች መንግስት መኖሪያ ቤቶችን በተከታታይ እያፈረሰ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በቦሌ ክ/ ከተማ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ እና በአራዳ ክ/ከተማ መኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸው ይታወሳል፡፡ –ኢትዮጲስመረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV